‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!››ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!!

“Ethiopia out of Oromia!” “Black Box in the OLF’s Belly” (ክፍል 1)  ሚሊዮን ዘአማኑኤል(ኢት-ኢኮኖሚ)

በኢትዮጵያ ሃገራችን የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ) የፖለቲካ ሴራ የተወጠነው በሻብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ በወያኔ መሪ መለስ ዜናዊና በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) መሪ ሌንጮ ለታ  ሲሆን የመቶ አመት የቤት ስራ ሰጥተናቸዋል፡፡ ጦርነቱን ከሰሜን ወደ መኃል ሃገር እናሸጋግረዋለን  ያሉት የዛሬ ሠላሳ አመት ነበር፡፡

የዘር ማፅዳት (ጀኖሳይድ) የሚዲያ የቅስቀሳ ሚና፡-

ጃዋር መሀመድ የሚመራው ኦኤምኤን ሚዲያ፣ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) የሚደጎመው የትግራይ ሚዲያ ሃውስ (TMH)፣ እንዲሁም የዲጂታል ወያኔ ደሞዝተኞች ለዘርና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ ኢትዮጵያውያን በግፍ እየተገደሉ፣ንብረታቸውና ኃብታቸው እየተዘረፈ ከኦሮሚያ ክልል እንዲወጡ ያደረጉ ሚዲያዎች ተጠያቂ ናቸው፡፡ የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ OMN በቀጥታ ስርጭቱ ሕዝብ እንዲነሳ፣ እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ ሲያስተላልፍ የትግራይ ሚዲያ ሃውስም በተመሳሳይ ድርጊት የOMNን ስርጭት ተቀብሎ በማሰራጨት አመጹ ላይ ነዳጅ በማርከፍከፍ ጀኖሳይዱን አቀጣጥለዋል፡፡ የፌዴራል መንግሥት የመገኛኛ ብዙሃን ህግና ደንብ እንዲከበር በማድረግ የድምጸ ወያኔ፣ የትግራይ ቲቪና የOMN፣ OBN እና ABC የሚዲያ ሥርጭት በህግ ተጠያቂ ናቸው እንላለን፡፡

የዘር ፍጅቱ ቅስቀሳ ውስጥ ‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!››…“Ethiopia out of Oromia!” ጅዋር መሃመድ

በኦኤምኤን የቴሌቪዝን ጣቢያው ቅስቀሳ ሥራን የተካውና የነጠቀው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ/ Oromia Broadcasting Network  (OBN)  ሲሆን በህዝብ ላይ የስነልቦና ጦርነት በማድረግ የኦሮሞን ህዝብና ኦነጋዊ ድርጅቶች የዘር ማፅዳት (ጆኖሳይድ) ቅስቀሳ በማስተጋባት ሚዲያው ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!›› የሚለው የፖለቲካ ሴራ ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! ሲሆን ዋና ዓላማው ኢትዮጵያውያነን ከኦሮሞ ክልል ማስወጣት ነው፡፡ በዘር ጥላቻ ንግግርና ቅስቀሳ የዘር ፍጅቱን የመሩት ምሁራን ውስጥ ‹‹ዲቃላ››ጁሃር መሃመድ፣ ‹‹መሬት እንጂ ሰው የለም›› ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ‹‹አትግዙ አትሽጡ አትለውጡ›› በቀለ ገርባ፣‹‹እንደሰባበሩን ሰባበርናቸው›› ሽመልስ አብዲሳ፣ “የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ከንቲባ መሆን ያለበት ኦሮሞ ብቻ ነው” ብርሃነመስቀል አበበ፣ ‹‹ደማቸው ውስጥ ያለው አማራ ብሔር እንጂ ›› ኩምሳ ዲርባ (ጃል መሮ)፣ ስሜን የቀየረብኝ ምኒልክ ነው!!!፣ ኮነሬል አበበ ገረሱ፣‹‹የኢትዮጵያ ቌንቌ ኢትዮጲኛ ይባል›› ህዝቅየል ጋቢሳ፣ ‹‹ክርስቲያን ማለት አማራ ነው አማራ ማለት ክርስቲያን ነው፡፡›› ዶክተር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት ከተናገሩት ‹‹ለኦሮሞ መሬቱ ማለት ማንነቱ ማለት ነው፡፡  ከአንድ ክፍለዘመን በላይ ሲሰደብ፣ሲጨቆን ሲፈናቀል የነበረው በመሬቱ ምክንየት እንጂ በማንነቱ ምክንያት አይደለም፡፡ በተለይም መሬት ለመምህራን ስንሰጥ፣ ለባለሃብቶች ስንሰጥ የከተማችን የህዝብ ስብጥር አይቀየርም ብላችሁ የምታስቡ ብትኖሩ ሁለት ሶስቴ ደጋግማችሁ አሰቡ፡፡  በዘፈቀደ (መሬቱን) አድለን አድለን ስናበቃ (ዶሞግራፊውን) ሲቀየር ለምን ተቀየረ ብለን መጮህ አንችልም፡፡ በኛው ውሳኔ ነዋ የተቀየረው፡፡ በርካታ ለውጦች የተመዘገበ ቢሆንም የመሬቱ ጉዳይን በተመለከተ ከተሞች ሥራቸውን በጥንቃቄ እንዲያከናውኑ ማሳሰቢያ የሰጡት  ደግሞ  ዶክተር አብይ አህመድ በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትር  ናቸው፡፡››

Ethio 360 Zare Men Ale “እንባ ወደ ደም ሲቀየር የተሰወረው እንባ ጠባቂ” Thursday April 08, 2021 – YouTube

 

‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› ወደ ‹‹ ኦሮሚያ የኢኮኖሚ ውድመት››

ብልፅግና/ኢህአዴግ  ዶክተር አብይ አህመድ መጋቢት ሃያ አራት ቀን 2010 ሥልጣን እንደያዘ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በቦሌ አየር ማረፍያ ቀይ ምንጣፍ አቀባበል ተደርጎለት በወለጋ ጫካ ሽምቅ ተዋጊ ሆኖ ከተወነ ጀምሮ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ፣ ሁለት ሽህ አምስት መቶ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በዶክተር አብይ አህመድ ዘመንም ፣ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ መሠረት በኦነግ  ሸኔ ዳቦ ስም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ‹‹ 707 (ሰባት መቶ ሰባት) ሰዎች መገደላቸው፣ 1344 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ አርባ አራት) ሰዎች በጥይት ተመተው የአካል ጉዳተኛ መሆናው ፣72 (ሰባ ሁለት) ሰዎች የመታፈናቸውን፣ እንዲሁም ሃያ ሥስት ባንኮች መዘረፋቸውን የተደበቀ ሚስጢር ይፋ አድርገዋል፡፡›› በዶክትር አብይ መንግሥት ኦነግ ከኤርትራ ምድር ከነበረው አምስት ሽህ ሽምቅ ተዋጊ ውስጥ አንድ ሽህ ሦስት መቶውን ብቻ ትጥቅ አስፈትቶ፣ ቀሪውን ሦስት ሽህ ሰባት መቶ ሠራዊት ከነትጥቁ አገር ውስጥ በማስገባት የወለጋ ህዝብ በኦነግ ሸኔና አባ ቶርባ ነፍሰ ገዳዬች መከራውን ያያል ይገኛል፡፡ አብዛኛዎቹ ታዳኞች የኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልፅግና ፓርቲ ሹማምንቶች በየቦታው እንደሚገደሉ፣ እንደሚቆስሉና  እንደሚታፈኑ  ታዉቆል፡፡ በኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ክልል በተለይ የወለጋ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ተይዞል፡፡ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ሽብርተኛነት ‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!›› የሚለውን ዘረኛ መፈክር  ከኦሮሚያ ምድር ብዙ ዜጎች በግፍ ተገድለዋል፣ ንብረትና ኃብታቸው ተዘርፎል፣ ብዙ ዜጎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ ከኦሮሚያ ክልል እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ በኦሮሚያ የህግ ሉዓላዊነት እስካልተከበረ፣ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል እስኪሆን ድረስ ትግላችን ሊቀጥል ይገባል፡፡ በኦሮሚያ ክልል መንግሥዊ ሽብርተኛነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የፈፀሙ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ ባለመቻሉ ወንጀሉ ቀጥሎ ህዝብ በስፋት ከኦሮሚያ ምድር በግፍ ተፈናቅሎ ወደ አማራና ቤኒሻንጉል  ክልሎች በመሰደድ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና ምርጫ ቦርድ በተቀነባበረ መልክ በተፈናቃዩ ስም ምርጫ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ህዝብ በስደት ላይ እያለ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለምርጫ ውድድር ሲቀሰቅሱ ለህዝብ መፈናቀልና ስደት ግድም አልሰጣቸው ይሄ ሁሉ የስብኣዊ መብቶች ጥሰት ሲከናወን ተከታትለው አለማጋለጣቸው ያሳዝናል፣ያሳፍራል፡፡ ምርጫ ቦርዱ በዚህ ወንጀል ይጠየቃል!!!

 

ኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)፣ ጁዋር መር የኦነግ ቄሮ፡-

‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!›› የኦሮሞ ፖለቲከኞች ፕሮጀክት በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ ጥሪ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ 123 (መቶ ሃያ ሦስት) ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ቢያንስ በ500 (አምስት መቶ) ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል። በኦሮሚያ ክልል ከአንድ ሺህ በላይ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ተነገረ። በመኖሪያ እና በንግድ ቤቶች ላይ የደረሰ ጉዳት፤በአሮሚያ ክልል፤ 523 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። 499 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ) መኖሪያ ቤቶች ፈርሰዋል፡፡  195 (መቶ ዘጠና አምስት) ሆቴሎች መቃጠላቸውን እና ሌሎች 32 (ሠላሳ ሁለት) ሆቴሎች ደግሞ በንብረት ላይ የመሰባበር ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም 104 (መቶ አራት) የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቃጠሎ ውድመት እንደደረሰባቸው አመልክተዋል። ስድስት አነስተኛ እና ግዙፍ ፋብሪካዎች በሁከቱ መቃጠላቸውን፣  የተቃጠሉ አነስተኛ ንግድ ቤቶች ቁጥር ድግሞ 232 (ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት) እንዲሁም የተሰባበሩት አስተኛ ንግድ ቤቶች አሃዝ 219 (ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ) መሆኑ ታውቆል፡፡ 232 (ሁለትመቶ ሠላሳ ሁለት) የግል እንዲሁም 12 የመንግሥት ተሸከርካሪዎች በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል። በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በምዕራብ አርሲ ሦስት ወራዳዎች  በተለይ በሻሸመኔ እና ባቱ ከተሞች እንዲሁም በባሌ ዞን ሮቤ እና አጋርፋ ከተሞች ገዳት ደርሶል። ‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!››  ማለት ኢትዮጵያዊያን ከኦሮሞ ምድር ይውጡ ነው፡፡

ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. የድምፃዊ ሃጫሉ አስከሬን ወደ አምቦ በመሸኘት ላይ እያለ ቡራዩ  ሲደርስ፣ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ተኩስ በመክፈትና አስከሬኑን በግዳጅ በማስመለስ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ጽሕፈት ቤት እንዲገባ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡ በዚህ ወቅት አንድ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባል መገደሉንና ሦስት መቁሰላቸውን፣ በአሥር ምስክሮች ማረጋገጡንና ከላይ በአቶ ጃዋር ምርምራ ላይ የገለጻቸው የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውን አስረድቷል፡፡ አብዛኛው የማስረጃ ዝርዝር በፎረንሲክ መረጋገጡን፣ ሁከት፣ ብጥብጥ፣ የሕይወት መጥፋትና ንብረት ውድመትን በሚመለከት በግልና በመንግሥት ተቋማት ላይ በአምስት ክፍላተ ከተሞች (በአዲስ አበባ) 200 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት መድረሱንም ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉ 43 ተጠርጣሪዎችን ቃል መቀበሉን፣ በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች ስለሞቱ ሰዎችና ስለወደሙ ተቋማት በደብዳቤ መጠየቁንና በአጠቃላይ ከአቶ ጃዋር ምርመራ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች ላይ ስለሚቀረው፣ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት መርማሪ ቡድኑ ጠይቋል፡፡››

 

‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!›› የኦሮሞ ፖለቲከኞች ፕሮጀክት በኦሮሚያን ክልል አድጎ የነበረው ኢኮኖሚና መሠረተ-ልማትን አጋዩት፡፡ ፋብሪካዎች ነደዱ፣ የአበባና የሰብል እርሻዎች ተቃጠሉ፣ መንግሥታዊ መዋቅሮች ፈረሱ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የመብራትና የውሃ፣ የትራንስፖርት መኪናዎች ወደሙ፣ ሆቴሎችና የቱሪዝም ሥፍራዎች በመቃጠላቸው እዛ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ኦሮሞ ሠራተኞች ልጆቻቸውን የሚያበሉት ዳቦ አጡ፣ የኦነግ ሽፍቶች እጃቸው በደም ታጠቡ፡፡  በኦሮሚያ መሠረተ-ልማቶች ወደሙ ክልሉ ለብዙ አመታት የገነባውን ኃብት አውድሞ በልማት ኃላቀር ክልሎች ጭራ እንዲሆን ያደረጉት የተማሩ የኦሮሞ ልጆቾ ከቦሌ አይሮፕላን እልል ብለን የተቀበልናቸው ሌንቾ ለታ፣ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ ፣ የጃል መሮ የኦነግ ሸኔ፣ የጁዋር መሃመድና የበቀለ ገርባ  የኦፌኮ  ፖለቲከኞች ያተረፈው ሞት፣እስራትና ስደት መሆኑን የኦሮሞ እናቶችና ልጆች ያውቃሉ፡፡

  • የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሃረር ከተሞች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ስር መካለል አለባቸው የህብረ-ብሔር የሆነውን ሁሉ ‹‹የኬኛ›› ፍልስፍና የእኔ የሚል የበሽታ ደዌ ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ፓርቲ  ከኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ምንድነው? ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ፓርቲ ከ መጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ ዶክተር አብይ አህመድ በትረ ሥልጣን ጨብጠዋል፡፡
  • የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ኦዴድ ብልፅግና የአዲስ አበባ ከተሞን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ በማድረግ የነደፉት የክልሎች ካርታ ታላቁን የፖለቲካ ሴራ ነዳፊዎች ሻብያና ወያኔ ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና መሆናቸው አዲሱ ትውልድ ሊያውቀው ይገባል እንላለን፡፡ 1889 እኤአ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና መዲና ሆና በእቴጌ ጣይቱ ተቆረቆረች፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ በዳግማዊ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ታላቁን የአፄ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት ከቆረቆሩ 132 (መቶ ሠላሳ ሁለት) ዓመታት አልፎታል፡፡
  • ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ፣የፌዴራል ፖሊስ ዋና ፅ/ቤት፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ፅ/ ቤቱን አዲስ አበባ ተደርጎል፣ ማዕከላዊ እዙ አዲስአበባ ሆኖ በመላ ኢትዮጵያ ፀጥታ የማስከበር ኃላፊነት ለኦሮሚያ ፖሊስ ተሰጥቶል፡፡ የኦህዴድ/ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የተረኝነት አገዛዝና አዲስ አበባን የመጠቅለል ‹‹ፌንፊኔ ኬኛ›› ስሜት የተሸጋገረበት ዓይን ያወጣ ዘረኛነት ይስተዋላል፡፡
  • ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግናበኦሮሚያ ክልል የኦሮሚያ ፖሊስ ስልጠና ለ30ኛ ለ40ኛ ጊዜ በብዙ ሽህዎች ተመርቆል፡፡ ከሜቴክ የ300 ሽህ የክላሽንኮብ መሣሪያ ከአንድ ሚሊዩን ጥይቶች ለኦሮሚያ ክልል ማስታጠቅ የዘረኝነት ፖለቲካ ለዘር ፍጅት ዝግጅት አንድ እርምጃ መሰናዶ ነው እንላለን፡፡ ይሄን ድርጊት፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ዝምታ ጊዜ ጠብቆ እዳ እንደሚያስከፍላቸው አንጠራጠርም፡፡
  • ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ሻብያ ኦነግ ትጥቁን ሳይፈታ በትግራይ በወያኔ በኩል በአቦይ ስብሃት ተባርኮ የገባውን ማስታወስ ብልህነት ነው እንላለን፡፡ የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር ከአስር ትንንሽ ወደ መቶ ትንንሽ ክልላዊ መንግስትነት በመከፋፈል በወሰንና ድንበር የማያባራ ጦርነትና ግጭት ከትቶ የእራሳቸውን ህልውና የማስጠበቅ የመቶ ዓመት ስውር የፖለቲካ ሴራን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘረኛ የጦር አበጋዞች ክልላዊ መንግስቶች እንደ አሸን በፈሉ ቁጥር የድንበርና የወሰን የጦርነት ግጭቶች እንደ ሰደድ እሳት ይዛመታል ጦሱም እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ፣ አፍጋኒስታ፣ ኢራቅ ህዝብ የጦር አውድማ፣ የማያባራ የውክልና ጦርነት መዛመቱን ማስታዋል ይገባል እንላለን፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተሰደው የመጡትን የሱማሌ፣የሶሪያና የየመን ዜጎችን እያየን ከእነሱ መማር የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡
  • በወርሃ ጥቅምት 2012ዓ/ም:- በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በጀዋር መሃመድ የተከብቤለሁ ድረሱልኝ ጥሪ ምክንያት በደሬዳዋ፣ ሀረርጌና ዶዶላ ከተሞች የሚገኙ ፅንፈኛ ቄሮዎች የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዶክተር አብይ መንግሥት አስታውቆል፡፡ ሜንጫ መር ቄሮዎች ብዙ ንብረቶች አውድመዋል፣ 25 ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡ 100 የኃይማኖት አባቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ከመቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ የዘር ፍጅቱ ያተኮረው በአመዛኙ በአማርኛ ተናጋሪዎች፣ አማሮች ከክልላችን ውጡልን በሚል ምክንያታዊ ዘረፋ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ በሌላ በኩልም በአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች በተለይም ለአማራ ያደሩ በሚል ተገድለዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች  የዘርና ኃይማኖት ፍጂት (ጆኖሳይድ)ሲል ጠቅላዩ ደግሞ  ‹‹ግጭት ነው!!!›› በማለት እንደ መብረቁ ብርሃናቸውን ቀድመው በመፈንጠቅ የህግ ሉዓላዊነትን ጣሱ፡፡
  • ሰኔ 23 ቀን 2012ዓ/ም፡- ‹‹የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮሚሽነር ግርማ ገላን መግለጫ መሠረት ‹‹በርካታ ኦሮሚያ ዞኖች በአርሲ፣ በጅማ ብሔር ተኮር ጥቃቶች ተፈጸመዋል፡፡ ከዛም አልፎ በአርሲ አካባቢ ላይ የተፈፀሙት የግድያ ወንጀሎች የሃይማኖት አዘል ንቅናቄዎች ነበሩ፡፡ በሃይማኖት ክርስቲያን እምነት ተከታዬች ኦሮሞ ሆነው የሞቱ በተለይ ምስራቅ አርሲ ሠላሳ አምስት ሰዎች ነው የሞቱት ከዚህ ውስጥ ሃያ ሁለቱ የሸዋ ኦሮሞ ተወላጆች ናቸው፡፡ ክርስቲያን በመሆናቸው የተገደሉ፡፡ አስራሦስቱ የአማራ፣ ደቡብ ክልል ተወላጆች መሆናቸው አረጋግጠናል፡፡››  ምንጭ፡-

https://www.youtube.com/watch?v=Cc9jO7RxdVs/ESAT ኢሳት ልዩ ዜና  16 July 2020

  • በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ ጥሪ የ123 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ቢያንስ በ500 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል። በኦሮሚያ ክልል ከአንድ ሺህ በላይ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ተነገረ። በመኖሪያ እና በንግድ ቤቶች ላይ የደረሰ ጉዳት፤በአሮሚያ ክልል፤ 523 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። 499 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ) መኖሪያ ቤቶች ፈርሰዋል፡፡  195 (መቶ ዘጠና አምስት) ሆቴሎች መቃጠላቸውን እና ሌሎች 32 (ሠላሳ ሁለት) ሆቴሎች ደግሞ በንብረት ላይ የመሰባበር ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም 104 (መቶ አራት) የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቃጠሎ ውድመት እንደደረሰባቸው አመልክተዋል። ስድስት አነስተኛ እና ግዙፍ ፋብሪካዎች በሁከቱ መቃጠላቸውን፣  የተቃጠሉ አነስተኛ ንግድ ቤቶች ቁጥር ድግሞ 232 (ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት) እንዲሁም የተሰባበሩት አስተኛ ንግድ ቤቶች አሃዝ 219 (ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ) መሆኑ ታውቆል፡፡ 232 (ሁለትመቶ ሠላሳ ሁለት) የግል እንዲሁም 12 የመንግሥት ተሸከርካሪዎች በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል። በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በምዕራብ አርሲ ሦስት ወራዳዎች  በተለይ በሻሸመኔ እና ባቱ ከተሞች እንዲሁም በባሌ ዞን ሮቤ እና አጋርፋ ከተሞች ገዳት ደርሶል። ኦህዴድ/ኦዴፓ ብልፅግና መንግሥታዊ ሽብርተኛነት በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊና ተጠያቂነት  ናቸው እንላለን፡፡
  • የአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሤ በዘዋይና ሻሸመኔ የገነባው ሦስት ኮከብ ሆቴል እንደወደመበትና  የጠፋው ንብረት 300 መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚገመትና 400 ሠራተኞች እንደነበሩት ገልፆል፡፡
  • በጅማ የአቶ ፀሐይ 100 ሚሊዮን ብር የገነቡት ሆቴል የወደመ ሲሆን ሆቴሉ 400 ሠራተኞች ነበሩት፡፡
  • በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ 38 የመንግሥት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል
  • አጋርፋ፡- ሰኔ 23 በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት የድጋፍ ሰልፍ እንወጣለን በሚል በተፈጠረው ሁከት በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን እንዲሁም ሰላሳ ስምንት የመንግሥት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ፣ በዚህ ድርጊትም ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት ሲቀሩ የወረዳው የመንግሥት መሥሪያ ቤት መውደማቸውን በንብረት ላይ የደረሰው ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት እንደሆነም፣ከሁከቱ ጋር በተያያዘ በተከሰተው ዝርፊያና ቃጠሎ ምክንያት ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን  የባሌ ዞን ፖሊስ ምርመራ ዲቪዚዎን ሃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ከበደ አስታወቁ፡፡
  • በመጋቢት ወር 2013 ዓ/ም በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ 303  ሰዎች መሞታቸውን፣ 369 መቁሰላቸውን እና በወረዳው ስምንት ቀበሌዎች 815 ቤቶች መቃጠላቸውን ለማወቅ ከእንባ ጥበቃ መረጃ ለማወቅ ተችሎል፡፡ እንዲሁም 91ሺህ 956 ሰዎች መፈናቀላቸውና የተፈናቀሉ ሰዎች ደብረብርሃን፣ አጣዬ፣ ኤፍራታ፣ ሸዋ ሮቢት ገንደ ውሃ፣ መሀል ሜዳ እና የተለያዩ ቦታዎች እንደሚገኙ ታውቆል፡፡
  • በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው በቦኔ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ “አሰቃቂና ዘግናኝ” መፈፀሙን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ረቡዕ ምሽት ላይ ይፋ እንዳደረገው በምዕራብ ወለጋ ውስጥ በሚገኘው በዚህ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ሰዎች 28 መሆናቸውንና ጉዳት የደረሰባቸው 12 መሆኑን ገልጿል።

መንግሥት ሃቀኛ ፍርድ ካልሠጠ ወደፊት በኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት እንደማይኖርና በባህር ማዶ ሃገራት አክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ‹‹ኢትዮጵያ ትውደም!!!›› እያሉ የኦሮሞ ህዝብን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርጉትን የፖለቲካ ሴራ የኦሮሞ ልጆች መመከት ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ በክልሉ የኢንቨስትመን ፍስት እንደቀነሰና የስራ አጥ ቁጥርም እንደጨመረ፣ የትራንስፖርት መኪኖች በፍርሃት እንደሌሉ፣ ንግድ መቀዛቀዙ ታውቆል፡፡  ኦነጎች የኦሮሞ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ተይዞ ለሞት፣ ለእስራትና ስደት ተዳርጎል፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ ድምፃቸውን ባጠፉ በወሩ ‹‹በቅረቡ በኦሮሚያ ክልል ለመናገር በሚያሳፍር መልኩ በርካታ ዜጎቻችን ሞተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግስት ይህን ተከትሎ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ኃላፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አብራርተዋል። በድርጊቱ ላይ የተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጠር ስር ውለዋል ብለዋል። ትናንት የተጸየፍነውን በደል ዛሬ ላይ የምንደግመው ከሆነ ከግጭት አዙሪት ልንወጣ አንችልም ሲሉም ነው የተናገሩት። ግጭቱን የብሔር መልክ እንዳለው አድርጎ የሚያራግቡ አካላት እንዳሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በግጭቱ በርካታ ኦሮሞዎች መሞታቸውን በአስረጂነት አንስተው፤ “ዋናው ነገር ግጭት ከተከሰተ መጀመሪያ የሚያጠቃው እኔን ነው የሚለውን መገንዘብ ያስፈልጋል” ብለዋል።

 

‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!›› የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሴራ ፕሮጀክት  ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ‹ብሄር ብሄረሰቦች› እጣ ፈንታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያ ክልለ ውስጥ የሚገኙ ሃያ አንድ የዞን አስተዳደር ከተሞች ውስጥ አዳማ፣ አንቦ፣ አሰላ፣ ባደሳ፣ ባሌ ሮባ፣ በደሌ፣ ቢሸፍቱ፣ ቤጊ፣ ቡሌ ሆራ፣ ጭሮ፣ ደንቢ ዶሎ፣ ፍቼ፣ ጊንቢ፣ ጎባ፣ ሃረማያ፣ ሆለታ፣ ጅማ፣ መቱ፣ ነገሌ አርሲ፣ ነቀምት፣ ሰበታ፣ ሻሸመኔ፣ እና ወሊሶ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በነዚህ ከተሞች ውስጥ ኦሮሞ ያልሆነ ህብረ ብሄር ህዝብ በቁጥር ስለሚበልጥ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሌላውን ህብረ ብሄር ህዝብ ከኦሮሞ ምድር ውጡ በማለት ልክ እንደ ሻሸመኔ ከተማን አቃጥለው፣ ሰዎች ገድለው፣ ንብረት ዘርፈውና አፈናቅለው በአደባባይ የፈጸሙትን ወንጀል በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን እጩዎች በመግደል፣ በመደብደብና በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት ሽመልስ አብዲሳ ለዚህ የዘር ማፅዳት (ጆኖሳይድ) ወንጀል በአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡

 

የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ምድር ይስፈን!!!

 

ምንጭ

(1)  ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንን ያሳዘነው ኢትዮጵያን የማፍረሱ ውጥን አሳዛኝና አንገት አስደፊ ክስተቶችን ትቶ አልፏል July 13, 2020

(2) በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ 38 የመንግሥት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል July 13, 2020

 

 

Leave a Reply