‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!››ከኦነግ ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! ቢሊዮነር ፍለጋ በጨረቃ!!! (ክፍል 2) ሚሊዮን ዘአማኑኤል(ኢት-ኢኮኖሚ)

“Ethiopia out of Oromia!” “Black Box in the OLF’s Belly” (ክፍል 2)  ሚሊዮን ዘአማኑኤል(ኢት-ኢኮኖሚ)

‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!››…“Ethiopia out of Oromia!”

 

ልማታዊ መንግሥት (Developmental State)፡-የመንግሥታዊው ዘርፍ 53 በመቶ፣ የግሉ ዘርፍ 47 በመቶ ብድር አገኙ፣ የአገሪቱ ባንኮች የሰጡት ብድር ከአንድ ትሪሊዮን ብር (25 ቢሊዮን ዶላር) ደረሰ፡-

ሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮችና 16ቱ የግል ባንኮች የሰጡት ከተበዳሪዎች የሚፈለግ የብድር መጠን፣ በሃያ በመቶ በመጨመር ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገጸ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰኔ የ2012 ዓ.ም. መጨረሻ ዓመታዊ ሪፖርት እንዳመለከተው፣ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ የደረሰው የብድር መጠን የተመዘገበ ነው፡፡ በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው በ2012 የሒሳብ ዓመት ተሰብሳቢ ሆኖ ከተመዘገበው ብድር ውስጥ 53 (ሃምሳ ሦስት በመቶ)፣ ወይም ከ530 (አምስት መቶ ሠላሳ) ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው ለመንግሥት ተቋማት የተሰጠ ነው፡፡ ከግሉ ዘርፍ የሚጠበቁት ተሰብሳቢ ብድሮች መጠን ደግሞ 484.4 (አራት መቶ ሰማንያ አራት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ይህም ባንኮች ከሰጡት ጠቅላላ ብድር ውስጥ 47 (አርባ ሰባት) በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በግሉ ዘርፍ ያልተሰበሰበው የብድር መጠን የ28.3 (ሃያ ስምንት ነጥብ ሦስት) በመቶ ዓመታዊ ዕድገት የታየበት መሆኑን የሚያመለክተው የብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ሪፖርት፣ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ከሆነው ብድር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው የማዕድን፣ የኃይልና የውኃ ዘርፍ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ከጠቅላላው ብድር ውስጥ ሦስቱ ዘርፎች 29.5 (ሃያ ዘጠኝ ነጥብ አምስት) በመቶ ድርሻ አላቸው ተብሏል፡፡  ከእነዚህ ቀጥሎ ከፍተኛ ብድር ያለበት ዘርፍ ኢንዱስትሪው ሲሆን፣ ከጠቅላላ ተሰብሳቢ ብድር ውስጥ 21.5 (ሃያ አንድ ነጥብ አምስት) በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይዟል፡፡ የዓለም አቀፍ ንግድ 13(አስራ ሦስት) በመቶ፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን 13(አስራ ሦስት) በመቶ፣ የአገር ውስጥ ንግድ 8.5(ስምንት ነጥብ አምስት) በመቶ፣ ትራንስፖርትና መገናኛ 6.7(ስድስት ነጥብ ሰባት) በመቶ፣ ሌሎች ደግሞ 9.6(ዘጠኝ ነጥብ ስድስት) ድርሻ እንዳላቸው የብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ (1)

የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ መንግሥታዊ ዘረፍ ወጪ በዶክተር አብይ የሦስት አመት አገዛዝ እየጨመረ መሄዱን በአንድ በኩል ለመንግሥታዊ ዘርፍ የተሰጠ ብድር 530 (አምስት መቶ ሠላሳ) ቢሊዮን ብር ሲሆን  በሌላ በኩል ለግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ የተሰጠው ብድር 484.4 (አራት መቶ ሰማንያ አራት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ብር ለግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ትኩረት አለመሰጠቱን ያሳያል፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ የሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprises) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው መክፈል ያልቻሉት 780 (ሰባት መቶ ሰማንያ) ቢሊዮን ብር ከንግድ ባንክ ተበድረው አለመክፈላቸው እየታወቀ ከወያኔ ኦዴፓ ብልጽግና መማር አልቻለም እንላለን፡፡ ኦዴፓ ብልጽግና ቦዘኔ ቢሊዮነር በጨረቃ እየፈለገ ይገኛል፣ ፋብሪካ ከፍቶ ሸቀጣ ሸቀጥ አምርቶ፣ እርሻ አርሶ ሰብል አምርቶ፣ የሥራ እድል የሚፈጥር ኢንቨስተር ከሃገራችን ምድር ጠፍቶል፡፡ በዚህም የተነሳ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ የመንግሥትና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶቸ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ እዳ ጨምሮል፣ አመታዊ የእዳ ወለድ የመክፈል አቅም ማጣፍያው ማጠር፣ የመንግሥታዊው ዘርፎች ወጪ ጨምሮል፣ የግብርና ታክስ መሰብስብ ችሎታ ዝቅተኛነት፣ ህዝብ በኑሮ ውድነት መሰቃየት የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርቶች የዋጋ ግሽበት  መናርና ሃገሪቱ በኮማንድ ፖስት ወታደራዊ አስተዳደር ወጪና በጦርነት ኢኮኖሚ ኪሳራ ተዘፍቃለች፡፡

 

 

‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››

‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› የኦቦ ለማ መገርሳና ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የኦሮሚያ ክልል ህዝብ በአዲሱ የኦሮሚያ ካቢኔ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››በሚል መርህ በኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዩት በፍጥነት ወደ ተግባር ለማስገባት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ባለሃብቶች ጥምረት ምክር ቤት መሥርቶ ወደ ልማት ለመገስገስ ተወጥኖ የኢኮኖሚ ፍኖተ-ካርታ ተቀርፆ በሥራ ላይ ውሎል፡፡ የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት መሠረት ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር/ኩባንያ አጠቃላይ ካፒታሉ በ1.6 ቢሊዩን ብር ሲሆን የክልሉ መንግሥት ለዚህ አክሲዩን ማህበር መመሥረቻ 500 ሚሊዩን ብር የመደበ ሲሆን ቀሪው ከአክሲዩን ሽያጭና ከባንክ ብድር መሆኑ አስታውቀው ነበር፡፡ አክሲዮኑ በመላ ኢትዮጵያ ዜጎች አልተሸጠም፣ ለኦሮሚያ ኢንቨስተሮች ብቻ መሆኑ ዘር ተኮር አሻጥር ነበር፡፡ ኢንቨስተርና ካፒታል ክልል የለውምና!!! ኬኛ ቤቬሬጅ (ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) በአክሲዩን ተመስርቶል፣እንዲሁም የኦሮሞ ኮንስትራክሽን አክሲዩን ማህበርና አምቦ ፕመር የተባለ የማዕድንና የግብርና ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር እንደሚመሠረት ተገልፆል፡፡ የኦሮሚያ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››የኦዳ ትራንስፖርት ኩባንያ በግማሽ ቀን በተካሄደ የአክሲዩን ሽያጭ 617 ሚሊዩን ብር የሚያወጡ አክሲዩኖች መሸጣቸው ይታወሳል፡፡ የኦዳ ትራንስፖርት የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት የተሸከርካሪዎች ግዥ በመፈፀም እንደሚጀምርና ከወጣቶች ጋር በጋራ የሚያስተዳድራቸው የነዳጅ ማደያዎችና የነዳጅ ዲፖዎች እንደሚኖሩት ተገልፆል፡፡ እንዲሁም ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› የኦህዴድ ዲንሾ የፓርቲ የንግድ ድርጅት የአሰላ የብቅል ፋብሪካ በመግዛት ሥራውን ጀምሮል ነበር፡፡ በኦሮሚያ ክልል ፍህታዊ የኢኮኖሚ ስርጭት የለም፣ አድሎዊ የኢንዱስትሪ ግንባታ፣ አድሎዊ የወንዜ ልጅነት በአርሲነት፣ አንቦ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጅማነት የፖለቲካ ካድሬዎች የሥልጣን ክፍፍል ሹኩቻ ቀጠለ፣ ኢፍህታዊ የባጀት ክፍፍል ለአለፉት 27 አመታት ተንሰራፍቶ መቆየቱ ቅሬታ አስነስቶ ነበር፡፡ በኦዴፓ ብልጽግና ዶክተር አብይ አገዛዝ ዘመን የምላሳዊ  መለስ ዜናዊ የ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› (Developmental State) ፅንሰ ሃሳብ ቀጥሎሏል፡፡

የኦዴፓ ብልፅግና ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› የሙስና ባህል ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2013ዓ/ም

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና ባለቤት አልባ ህንፃዎች እንዲሁም ኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ዙሪያ የተደረገ የማጣራት ውጤት መሠረት በሃገራችን የተፈለፈሉ ህጋዊ ቦዘኔ የንግድ ባንክ ማናጀሮች ባጫ ጊኒ ባንክ ዘርፎ ለኦሮሞ ኢንቨስተሮች ገንዘብ ያበደረና፣ በህገወጥ መንገድ ሃያ ሦስት ባንኮች የዘረፈ የወለጋው ጃል መሮ እንኳን ገንዘብ የሰዎች አንገት እያረዱ፣ ህፃናት፣ ሴቶች፣ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች እየገደሉ ምንም ፍርድ ያላገኙ  የምስኪን ደሃዎች እንባ እንኳን መሬቱን ነፍሱን ሰርቃችኃልና ፈጣሪ ይፋረዳችኃል እንላለን፡፡

  • በአዲስ አበባ ከተማ 1,338 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ ሠላሣ ስምንት) ሄክታር መሬት በሕገ-ወጥ የተወረረ መሆኑን፣ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በሦስት አመት ይሄን ሁሉ ከዘረፈ ምርጫ ከተመረጠ ሃገሩን ይሸጣል!!!
  • በአዲስ አበባ ከተማ 21,695 (ሃያ አንድ ሽህ ስድስት መቶ ዘጠና አምስት) የጋራ መኖርያ ቤቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን፣ ከዚህ ውስጥ 15,891 (አስራ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አንድ) የሚሆኑት የባለቤትነት መረጃ አልቀረበባቸውም። 850 (ስምንት መቶ ኃምሳ) ቤቶች ደግሞ ዝግ ሆነው ሲገኙ 4,530 (አራት ሺህ አምስት መቶ ሠላሳ) ባዶ ሆነው ተገኝተዋል። በሕገ-ወጥ መልኩ በግለሰቦች ተይዘው የሚገኙ 424 (አራት መቶ ሃያ አራት) ሲሆን በዕጣ ሳይሆን በተለያዩ አግባቦች ወደ ተጠቃሚው ግለሰቦች የተላለፉ ደግሞ 51,064 (ሃምሳ አንድ ሺህ ስልሳ አራት) ቤቶች ሆነው ተገኝተዋል።
  • በአዲስ አበባ ከተማ 322 (ሦስት መቶ ሃያ ሁለት) ግንባታቸው ያለቀና ያላለቀ ህንፃዎች ባለቤት አልባ ሆነው መገኘታቸውን፣ ባዘኔ ኢንቨስተሮች የገነቡትን ዓየር በዓየር ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በግልፅ ጫረታ ይሸጡ፡፡
  • በአዲስ አበባ ከተማ ለመኖርያና ለንግድ የተከራዩ 14,641 (አስራ አራት ሽህ ስድስት መቶ አርባ አንድ) የቀበሌ ቤቶችን ያለ አግባብና በሕገ-ወጥ ይዞታነት የሚገኙ መሆኑን አስታውቀዋል።
  • በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 13,389,955 (አስራ ሦስት ሚሊየን ሦስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አምስት ካሬ ወይም 1,338 (አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ስምንት) ሄክታር መሬት በሕገ-ወጥ መያዙን አስታውቀዋል። ሌቦቹ ፍርድ ቤቱንም ስለሰረቁት በሃገሪቱ ውስጥ ፍትህ የለም!!!

 

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprise)፡-

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ከህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት መንግሥታዊ ዘርፍ ኢንቨስትመንት በማስፋፋት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር በመውሰድ አትራፊነታቸው ያልተረጋገጠ ፕሮጀክቶች በመገንባትና የግሉ ዘርፍ ሊሰራቸው የሚችሉትን ሥራዎች በመሻማት ዘለቄታና ቀጣይነት የሌላቸው ፕሮጀክቶች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ የሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ ዘመን 780 ቢሊዩን ብር እዳ ያለባቸው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ልብ ሊሉ ይገባል፡፡  የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ኢንቨስትመንት፡- በኦሮሚ ክልል የግል ኢንቨስትመንት ባለመኖሩ የተነሳና ብዙ ኢንቨስተሮች ከክልሉ መውጣት ዋና ምክንያት ንብረትና ኃብታቸው የወደመባቸው ባለኃብቶች ከመንግሥት ምንም ካሣ ባለማግኘታቸው ነው፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መንግሥት መር ኢንቨስትመንት

  • የኦሮሞ ክልል ፍርድ ቤት በ1.8 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሚሊዮን) ብር፣
  • የኦሮሚያ ፖሊስ ፅህፈት ቤት በ700 (ሰባት መቶ) ሚሊዮን ብር፣
  • ለኦሮሚያ ጀግኖች መታሰቢያ አንድ ቢሊዩን ብር በጠቅላላው ሦስት ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ብር በማውጣት መንግሥት መር ኢንቨስትመንት እድገት ጨምሮል፡፡

ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር ODAA Integrated Transport S.C.

ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር በትራንስፖርት የንግድ ዘርፍ ሃምሳ አገር አቆራጭ አውቶብሶች በመግዛትና ሁለት የቤንዚን ማደያ ጣቢያዎች በመገንባት የተጀመረ የኦሮሞ ክልል መንግሥት ንብረት ነው፡፡  ኦዳ ከቮልቮ የሲውድን ካንፓኒ አንዱን አውቶብስ በ5.8 (አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሽህ) ብር ዋጋእንዲሁም ሃምሳ አውቶብሶች በ400 (አራት መቶ) ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ዋጋ ገዝቶል፡፡ ኦዳ በገላን ሁለት የቤንዚን ማደያ ጣቢያዎች በ42 (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ብር ወጪ ገንብቶል፡፡ኦዳ በሚቀጥሉት ሦስት አመታት ውስጥ መቶ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች  ለመገንባት አቅዶል፡፡ (2)

“ODAA Integrated Transport S.C, officially start operation in the transportation business with 50 cross country buses and two gas stations. Shimele Abdisa, Oromia Regional President, Addisu Arega, ODP Central Office Head, Deputy Mayor Engineer Takele Umma and other state officials were attending the launching ceremony yesterday. The company bought the buses from Volvo, a Swedish car assembler, for 400 million Br. Having 55 seats and equipped with Wi-Fi services and televisions, each bus cost the company 5.8 million Br. In addition, ODAA has also inaugurated two fuel stations that are built-in Gelan with a cost of 42 million birr. The Oda Integrated Transport Service is also planning to build 100 gas stations over the next three years. The two gas stations will serve 24 hours, creating jobs for 100 people, said Eshetu Zeleke, General Manager, ODAA Integrated Transport Services Association.”

ኬኛ ቤቬሬጅ (ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) Kegna Beverages

ኬኛ ቤቬሬጅ (ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) በኦሮሚያ ክልል የኢኮኖሚ አብዬት ለማምጣት ከጀርመን ካንፓኒ ጋር በ2017 እኤአ ስምምነት ተፈራረመ፡፡  ኬኛ ቤቬሬጅ በጊንጪ ከተማ የሚገነባ ሲሆን 5.5 (አምስት ቢሊየን አምስት መቶ ሚሊዮን) ብር የግንባታ ወጪ የሚሰራ ሲሆን አንድ መቶ አንድ ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው ያርፋል፡፡ ኬኛ ቤቬሬጅ ቢራ፣ ለስላሳ፣ ጭማቂ፣ የታሸገ ውኃ ያመርታል፡፡ ኬኛ በሙሉ አቅሙ ሲሰራ ሦስት ሚሊዮን ሄክቶሊትር በዓመት ያመርታል፡፡ ለሦስት ሽህ አምስት መቶ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡  ኬኛ ቤቬሬጅ  አምስት ሽህ የአክሲን ባለድርሻ ባላቸው የተመሠረተ ሲሆን 1.5 (አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን) ብር ካፒታልና 700 (ሰባት መቶ) የተከፈለ ተቀማጪ ብር  የተመሠረተ ካንፓኒ ነው፡፡ (3)

German Firm Secures Deal to Build Kegna Beverages/July 20 , 2019

Kegna Beverage S.C, one of the companies that followed the economic revolution in Oromia Regional State in 2017, has signed a deal with a German company for the construction of a plant. The plant will be built at Ginchi town with 5.5 billion Br in investment. The agreement will enable Kegna to outsource the project, and the German company will oversee the feasibility study, development, design and construction of the plant, as well as the installation of the machinery. The plant, occupying 101ha of land, will produce beer, juice, bottled water and soft drinks. At full capacity, the plant will produce three million hectolitres a year and create job opportunities for 3,500 people. Other projects under the economic revolution include Oda Integrated Transport, Kegna Agricultural Machinery and Welabu Construction. Kegna has around 5,000 shareholders including farmers, 1.5 billion Br in subscribed capital, of which 700 million Br is paid-up.

ኬኛ የግብርና ትራክተር መገጣጠሚያና ማሽነሪዎች Kegna Agricultural Machinery

ኬኛ የትራክተር መገጣጠሚያ ማሽነሪ በሻሸመኔ ከተማ በ37000 ስኩየር ሜትር  ላይ የተገነባ ፋብሪካ ሲሆን በሃምሳ ሠራተኞች ሃያ ትራክተሮች  በቀን የመገጣጠም አቅም እንዳለው፣ በቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት ለማ መገርሳ ተገልፆ ነበር፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አንዱ ክንፍ የሆነው ኬኛ የግብርና መሣሪያዎች ማኑፋክቸሪንግና ጠቅላላ ንግድ  ድርጅት ትራክተሮች በመገጣጠም እንዲሁም የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ባንክ በብድር አቅርቦት ለተደራጁ የኦሮሚያ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር የኦሮሚያ ክልል መንግሥት 350 ሦስት መቶ ሃምሳ ትራክተሮችን 285 በሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ሚሊዮን ብር  ብድር  ለወጣቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡ 1750 ወጣቶች በሚቀጥሉት አራት ወራቶች ውስጥ ትራክተሮቹ እንደሚከፋፈሉ ታውቆል፡፡ የመጀመሪያው መቶ ትራክተሮች ለአምስት መቶ ወጣቶች በሽመልስ አብዲሳ ተከፋፍሎል፡፡ የጆን ዲር ትራክተር የአንዱ ዋጋ 813000 ብር ሲሆን ለአምስት ወጣቶች አስር በመቶ ገንዘብ ከፍለው ቀሪውን በአምስት አመታት ውስጥ በባንክ በስምንት በመቶ ወለድ ይከፍላሉ ፡፡ ኬኛ የትራክተር መገጣጠሚያ ማሽነሪዎቹን ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት የውጪ ምንዛሪ ዶላር ከየት ያገኝ ይሆን ዋነኛ ጥያቄአችን ሲሆን የፕሮጀክቱ አዋጭነት ጥናት  ምን ያህል አስተማማኝ እንደሆነ የተባለ ነገር የለም፡፡  (4)

Regional State Provides Unemployed Youth with Tractors:-Kegna Agricultural Equipment Manufacturing & General Trading, part of the economic wing of the Oromia Regional State, assembled the tractors, while Oromia Savings & Credit Institution will finance the tractors through a credit arrangement. As part of an effort to create job opportunities, the Oromia Regional State has provided organised groups of youth with 350 tractors worth 285 million Br in a loan arrangement…Oromia Industry & Enterprises Development Council, which aims at creating 1.1 million jobs in the regional state this year, will oversee the project. It also coordinated and organised the youth and work through Oromia Savings & Credit Institution to facilitate the credit. The tractors will be entirely handed over to 1,750 youth in the coming four months. The first 100 tractors were delivered to 500 youth two weeks ago with a ceremony that was held in Shashemane town with the presence of Shimeles Abdisa, deputy administrator of the Oromia Regional State. Having 75 horsepower, the John Deere tractors have a unit price of 813,000 Br. Tractors were provided to groups with five members, who are expected to raise 10pc of the value in advance. The Oromia Savings & Credit Institution will cover the remaining cost, and the youth are expected to pay back the loan within five years along with eight percent interest…

ኬኛ የትራክተር መገጣጠሚያ ማሽነሪ 390 በሃገር ውስጥ የተገጣጠሙ 310 ትራክተሮችና 80 የማጨጃ ኮምፓይነሮች  በሽመልስ አብዲሳ ለገበሬዎች የተሰጠ ሲሆን ሠላሳ በመቶ ቆጥበው በመክፈል እንዲሁም ቀሪውን 70 በመቶ በአምስት አመታት ውስጥ ለባንክ ለመክፈል የክልሉን የግብርና ምርት ከፍ ለማድረግ የታቀደ ፕሮጀክት ነው፡በግሉ የግብርና ዘርፍ ትራክተሮችና የማጨጃ ኮምፓይነሮች የሚያከራዩ የንግድ ድርጅቶች ከሥራ ውጭ የሚያደርግ ፕሮጀክት ዘላቂነትና አስተማማኘነት የለውም የውጪ ምንዛሪ፣ መለዋወጫ እቃዎችና የሰለጠኑ የቴክኒክ ሰዎች ችግር ፕሮጀክቱ ዘላቂነትና ቀጣይነት እንደሌለው ያታመናል፡፡ ኬኛ የትራክተር መገጣጠሚያ ማሽነሪ ከተመሰረተበት 2018 እኤአ ጀምሮ 730 ትራክተሮችና ኮምፓይነሮች ማከፋፈሉ ታውቆል፡፡ በርክክብ ሥነስርዓቱ ላይ ሽመልስ አብዲሳና የብሄራዊ ባንክ ገዥው ዶክተር ይናገር ደሴ  ተገኝተዋል፡፡ (5)

“Out of the total machinery 310 are Tractors while the remaining 80 are combine harvesters.

The farmers have covered 30 pct of the price through saving, and are required to pay the remaining 70 percent gradually in five years, it is sated on the handover ceremony…Kegna Agricultural Equipment Manufacturing has distributed 730 machineries including today’s tractors and combines to farmers since its commencement in 2018..High ranking government officials including governor of the National Bank of Ethiopia, Dr. Yinager Dessie attended the handover event.”

‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!››…“Ethiopia out of Oromia!”

በሻሸመኔ ከተማ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ላይ ለተፈፀመ ወንጀል የኦሮሞ ክልል መንግሥት ካሣ አልከፍልም አለ፡፡ የወደመው ንብረት የአማራ፣ ጉራጌ፣ ትግራይ፣ የደቡብ የወላይታ ወዘተ ንብረትና ኃብት በመሆኑ እንደሆነ ህዝብ ያውቃል፡፡ በኦሮሚያ ክልል 523 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። 499 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ) መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ተሰባብረው ምንም ካሳ አልተከፈላቸውም፡፡በሻሸመኔ ከተማ  195 (መቶዘጠና አምስት) ሆቴሎች መቃጠላቸውን እና ሌሎች 32 (ሠላሳ ሁለት) ሆቴሎች ንብረት ተሰባብሮል ምንም ካሳ አልተከፈለም፡፡በሻሸመኔ ከተማ 104 (መቶ አራት) የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ ስድስት አነስተኛ እና ግዙፍ ፋብሪካዎች በሁከቱ ጋይተዋል ምንም ካሳ አልተከፈለም፡፡ የተቃጠሉ አነስተኛ ንግድ ቤቶች  232 (ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት) ሲሆኑ እንዲሁም የተሰባበሩት አስተኛ ንግድ ቤቶች 219 (ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ)  ምንም ካሣ አልተከፈላቸውም፡፡ በተመሳሳይ 232 የግል እንዲሁም 12 የመንግሥት ተሸከርካሪዎች በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል። በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በምዕራብ አርሲ ሦስት ወራዳዎች ውስጥ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፤ በተለይ በሻሸመኔ እና ባቱ ከተሞች እንዲሁም በባሌ ዞን ሮቤ እና አጋርፋ ከተሞች የደረሰው ገዳት  ከፍተኛ መሆኑ ታውቆል።

 

ምንጭ፡-

Leave a Reply