
ኢትዮጵያ ከግጭት በኋላ የምታደርገውን መልሶ ግንባታ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለአገሪቱ ሰላም ሂደት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ክብር ለመስጠት አዲስ አበባ ላይ የዕውቅና ዝግጅት ማካሄዱ ይታወሳል ፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሹዌ ቢንግ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የእውቅና ሰርተፍኬት ተቀብለዋል ።
ኢትዮጵያ ካለፈው ዓመት ህዳር ወር ጀምሮ የውስጥ ውዝግቧን ገታ አድርጋ የሰላም ሂደት መጀመሯ ጥሩ መሻሻል መሆኑን የጠቀሱት ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ‹‹ይህ የአንድነት ድል ነው›› ብለዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የሚደረግ ውይይት የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ጥቅም የሚያስከብር እንደሆነ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ቁልፍ ሚና እንደምትጫወት የገለጹት ማኦ ሰላም ያላት እና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለቀጠናው ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ትልቅ ፋይዳ አላት ብለዋል ሲል ዥንዋ ዘግቧል ።
“ቻይና ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት በጽኑ ትደግፋለች። ከዚሁ ጎን በድርድር ሰላም ለማምጣት እና መግባባትን ለመፍጠር በንቃት ስንሰራ ቆይተናል” ብለዋል ማኦ።
ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
Source: Link to the Post