ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ወደቦች የቁም እንስሳትን ኤክስፖርት ለማሳደግ እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ የከፍተኛ ሚኒስትሮች ልዑካን…

ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ወደቦች የቁም እንስሳትን ኤክስፖርት ለማሳደግ እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ የከፍተኛ ሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ትናንት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ከፊል ራስ ገዝ የሆነችዉ ፑንትላንድ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ለቁም እንስሳት ኤክስፖርት የሚሆኑ ቦታዎችን ለመጎብኘት መምጣቱም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በፑንትላንድ ፋይናንስ ሚኒስትር ሞሃመድ ፋራህ ሞሃመድ የተመራዉ ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያ ሲገባ በዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በዉይይቱ ወቅት ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ እና በፑንትላንድ መካከል ያለዉን ባህላዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት ትኩረት የሰጠበት ጉዳይ ነበር የተባለ ሲሆን፤ በደህንነት እና በትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያ ለምታደርገዉ ድጋፍም ምስጋናቸዉንም አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር የጠነከረ ግንኙነት እንዲኖራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዉ፤ በሁለቱ አገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም አስታዉቀዋል፡፡

ይህ ጉብኝት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት በሻከረበት በዚህ ወቅት የተደረገ ብቻ ሳይሆን፤ ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድም ከሶማሊያ መንግስት ጋር ዉጥረት ዉስጥ በገባችበት ወቅት የተደረገ ጉብኝት ነዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

Source: Link to the Post

Leave a Reply