ኢትዮጵያ ካላት  የማዕድን ሀብት 90 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ተቋማት ናቸው የሚጠቀሙት ተባለ።ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ የማዕድን ሀብት ውስጥ 10 በመቶ ብቻ እንደምትጠቀም እና 90 በመቶ የሚሆ…

ኢትዮጵያ ካላት  የማዕድን ሀብት 90 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ተቋማት ናቸው የሚጠቀሙት ተባለ።

ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ የማዕድን ሀብት ውስጥ 10 በመቶ ብቻ እንደምትጠቀም እና 90 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ተቋማት ለራሳቸው ጥቅም አንደሚያውሉት ታውቋል።

የኢጂሲ ግሎባል ትሬዲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ መዓዛ ገ/መድህን  ሀገራችን የከበሩ መዓድናት ሀብት ባለቤት ስትሆን ከዘርፉ የሚገባትን እየተጠቀመች አይደለም ብለዋል ።

ወ/ሮ መዓዛ ይህን ያሉት ድርጅታቸው በከበሩ ማእድናት ዙሪያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ባስመረቀበት ወቅት  ነው።

ኢጂሲ ግሎባል ትሬዲንግ የስልጠና ማእከል  ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ ወደስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዙሮች በከበሩ ማእድናት ዙሪያ ያሰለጠናቸውን 80 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል ።

ይህ የስልጠና ማዕከል  በሀገራችን  የመጀመሪያው ነውም ተብሏል ።

የኢጂሲ ግሎባል ትሬዲንግ ዋና ስራ ሲኪጅ ወ/ሮ መዓዛ ገ/መድህን በሀገራችን ከ40 በላይ የተለያዩ የከበሩ ማዕድን ያሉ ቢሆንም የሚገባትን ሃብት  ከዘርፉ አልተገኘም  ብለዋል።

ለዚህም ምክንያት በዘርፉ በቂ የሆነ የሰለጠነ የሰው ሃይል ባለመኖሩ ነው ተብሏል።

የኢጂሲ ግሎባል ትሬዲንግ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ይትባረክ ነጋ  ፤በሀገራችን ካሉት በርካታ ማዕድናት መካከል 90 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ተቋማት የሚጠቀሙ ሲሆን ኢትዮጵያ 10 በመቶውን ብቻ ነው መጠቀም የቻለችው ብለዋል።

በዚህም ድርጅታቸው በከበሩ ማእድናት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በዘርፉ የተማሩና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በመፍጠር ረገድ እየሰራ እንደ ሚገኝም ተናግረዋል ።

ኢጂሲ ግሎባል ትሬዲንግ የስልጠና ማእከል በ2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ህጋዊ ዕውቅና ፈቃድ አግኝቶ በከበሩ ማእድናት ዙሪያ ተማሪዎችን ለማሰልጠን የተቋቋመ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነዉ።

በልዑል ወልዴ

ሚያዝያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply