ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋት የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የመነጨ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋት የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የመነጨ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ወገኖች ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋታቸው የማይሆን እና የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የሚመነጭ መሆኑን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የኢትዮጵያ ወዳጆች በሃገሪቱ ስላለው ሁኔታ ለሰጡት ትኩረት መንግስት ደስተኛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋታቸው የማይሆን እና የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ ካለመረዳት የመነጨ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

አሁን እየተካሄደ ያለው ህግ የማስከበር ስራ ሰላምንና መረጋጋትን በማስፈን ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ህግ የማስከበሩ ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

The post ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋት የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የመነጨ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply