ኢትዮጵያ ውስጥ በቅድመ መደበኛ፣ በመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ያሉ17 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን ዩኒሴቭ (UNICEF) አስታወቀ።ዩኒሴፍ 3.5 ሚሊዮን የሚገመቱ በአ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/WGXZK0W6krQiysOuYgv-G1uoGrPbTmlQo8FUWC1au1kdRxGxTxgjdErafCITJ3i6MfGB820VMi4gbXgD8bUz1f29KrVpstgLQkMb6DdBrD1laKrU7DuxKp0MgTabcxo-vpynpwbBWS3WX_pXrM0KZC67SJQnL_mcj3SIvsB4Bx3d-hWVP75NJTTJidtbQ9uN-BrcZmRn-a4O0bdNDMlnL7ojGQgJwDlqOQFUt4vKad0-iK2iVPaWRdGl4xjspJBu5eS-eytoDHRwncCQDrHQ6QULb1uatdQCB-nIZuTPUxzuRYU6Qw5hsx23VNVsWqK-YvaGWX5nStj5-3DgFI02jA.jpg

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅድመ መደበኛ፣ በመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ያሉ17 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን ዩኒሴቭ (UNICEF) አስታወቀ።

ዩኒሴፍ 3.5 ሚሊዮን የሚገመቱ በአንደኛ ደረጃና በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙ ሕፃናት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ሥጋት መጋለጣቸውንና ይህም ትምህርት ላይ የተጋረጠውን ቀውስ የበለጠ ማባባሱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት “ችግር ፈቺ ያልሆነ፣ የሀገሪቱን ኑሮ እና ተጨባጭ ጉዳዮች የማይመለከት መሆኑ” በውጤትም ሆነ በጥራት ማሽቆልቆል እየታየበት መሆኑን አንድ የትምህርት ባለሙያ ተናግረዋል።

በጦርነትና ግጭት ክፉኛ እየተጎዳ ያለው የኢትዮጵያ የትምህርት ሁኔታ፤ ከዚያም ያለፉት የመንግሥት ሠራተኞች በደሞዝ ማነስ እየተፈተኑ ለትምህርት የሚሰጠውን ዋጋ እየጌዳ ስለመሆኑ ይነገራል።

ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ ከጠቅላላ ትምህርት ሰጪ 47 ሺህ ገደማ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸው የላቁት አራት ናቸው ማለቱ ባለፈው ዓመት የተሰማ አስደንጋጭ እውነታ ሆኖ አልፏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ሕፃናት ትምህርትን ለማረጋገጥ ጥረቶችን እንደሚመራ ያስታወቀው የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት መርጃ ማዕከል ትናንት ባወጣው መረጃ ደግሞ 17 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንሕፃናትና ታዳጊ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።

ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply