ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ነው ባሉት የሰብአዊ ቀውስ ምክንያት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ትእዛዝ ሰጡ።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ…

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ነው ባሉት የሰብአዊ ቀውስ ምክንያት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ትእዛዝ ሰጡ።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ፣የአማራ ክልል ባለስልጣናት ፣ የህወሓት አመራሮች እና የኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ (executive order) የትግራይ ክልል ግጭት እንዲራዘም ፤ ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይቀርብ ያስተጓጎሉ እና የተክስ አቁም ስምምነት እንዳይደረስ እንቅፋት ሆነዋል ባሏቸው ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ወስነዋል።

ማዕቀቡ እንዲጣል ያዘዙትም ከላይ ለተጠቀሱት ጉዳዮች ተጠያቂ ናቸው በተባሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የአማራ ክልል መስተዳደር ባለስልጣናት ላይ፤ እንዲሁም በህወሓትና በኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ እንደሆነ የአሜሪካ መንግስት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

ተጠያቂ ናቸው የተባሉት የመንግስት ባለስልጣናት እና የህወሓት አመራሮች ማንነት ግን ይፋ አልተደረገም።
ይሁን እንጂ የአሜሪካ የመንግስት ግምጃ ቤት ከአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር ተጠያቂ መሆን የሚገባቸውን እየለየ ማዕቀቡን ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ማዕቀቡ በተመረጡ ግለሰቦች ላይ ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግ እና የኢትዮጵያ ህዝብን በማይጎዳ መልኩ እንደሚተገበር የአገሪቱ መንግስት ያወጣው መግለጫን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply