ኢትዮጵያ የላሙን ወደብ ልትጠቀም ነዉ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4፣ 2013 የኬንያ መንግስት የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገለጸ:: የኬንያ መንግስት የላፕሴት ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገልጿል። የላፕሴት ኮሪደር ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሚኒስትር ሜና አኬንዶ በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ጉብኝት በማድረግ ከአምባሳደር መለስ ዓለም ጋር ተወያይተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው የኢትዮጵያ እና የኬንያ የግል ባለሀብቶች የላሙን ወደብ መጠቀም እንዲችሉ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የወደቡ አገልግሎት በተመለከተም በኢትዮጵያ የማስተዋወቅ ሥራ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ኃላፊው ጠቁመዋል። አምባሳደር መለስ ዓለም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ኢትዮጵያ እና ኬንያን የበለጠ
ማስተሳሰር የሚችሉ ሶስት ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

እነዚህም የላሙ ወደብ ምርቃት፣ የሞያሌ የአንድ ኬላ አገልግሎት ሥራ መጀመር እና የኬንያው ሰፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃድ ማግኘት ዋና ዋናዎች እንደሆኑ አምባሳደር መለስ አሰረድተዋል። የኬንያ ባለሀብቶችም በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የኢንቨስትመንት እድል እንዲጠቀሙ በማድረግ የላሙን ወደብ አገልግሎት ማስተዋወቅ ያስችላል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply