ኢትዮጵያ የባህር ሃይሏን ለማልማት የፈረንሳይን ድጋፍ እንደምትፈልግ ገለጸች፡፡

በዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ ያለችዉ አገራችን ለባህር ሃይል ልማት ፊቷን ወደ ፈረንሳይ ማዞሯ ተገልጿል፡፡

በቀይ ባህር አከባቢ ያለዉ ዉጥረት ኢትዮጵያ ለአጠቃላይ ደህንነት በስፍራዉ የባህር ሃይሏን ለማሰማራት እንድታስብ አድርጓታል ነዉ የተባለዉ፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጪ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ፤ በፈረንጆቹ ጥር 17 ከፈረንሳይ ብሔራዊ መከላከያ እና የጦር ኃይሎች ብሔራዊ ምክር ቤት ኮሚቴ ተወካዮች እና ከቋሚ ኮሚቴዉ አባላት ጋር በተደረገ ስብሰባ ላይ ነዉ ይህን ሀሳብ የተናገሩት፡፡

በስብሰባዉ ላይ ኢትዮጵያ በተለያዩ የሰላም ማስከበር ዘመቻዎች ላይ መሳተፏን በማንሳት ለአህጉሪቱ ያላት ጥቅም ከፍ ያለ ነዉ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ 5ተኛዋ የፈረንሳይ ትልቅ ገበያ ስትሆን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ደግሞ ሁለተኛው ትልቁ የንግድ ትርፍ የሚገኝባት ናት።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያን በጎበኙበት በመጋቢት 2019 የዉትድርና ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በዚህም ከፈረንሳይ ወደ ኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያም ወደ ፈረንሳይ በተመሳሳይ ወታደሮችን ለመላክ እና በጅቡቲ ሰፍረዉ የሚገኙ የፈረንሳይ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

በፈረንሳይ ድጋፍ የኢትዮጵያን የባህር ኃይል ክፍል ለማቋቋምም የፍላጎት ደብዳቤ ተፈርሟል ነዉ የተባለዉ።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply