ኢትዮጵያ የተካተተችበት የመጀመሪያዉ የብሪክስ ስብሰባ በሞስኮ በመካሄድ ላይ ነዉ፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የተካተተበት የመጀመሪያዉ የብሪክስ ስብሰባ በሩሲያዋ ዋና ከተማ ሞስኮ በመካሄድ ላይ ይገ…

ኢትዮጵያ የተካተተችበት የመጀመሪያዉ የብሪክስ ስብሰባ በሞስኮ በመካሄድ ላይ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተካተተበት የመጀመሪያዉ የብሪክስ ስብሰባ በሩሲያዋ ዋና ከተማ ሞስኮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ እና ግብጽ የተካተቱበት እና መስራች አገራት ሩሲያ፣ ቻይና ፣ብራዚል፣ ህንድ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉበት የመሪዎች ጉባዔ በሞስኮ በመካሄድ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

የብሪክስ ቡድን በ2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 በማደግ ላይ ያሉ አገራትን መቀበሉ የሚታወስ ነዉ፡፡

ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉት አምስት አገራት እና መስራች አገራት በሩሲያ ሞስኮ እየተደረገ ባለዉ ስብሰባ ላይ በምክትል የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸዉ መወከላቸዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የብሪክስ አባል አገራት ከ10 ዓመታት በፊት ደቡብ አፍሪካ ወደ ቡድኑ ከተቀላቀለች በኋላ ነዉ በ2024 እነዚህን አምስት አገራት የተቀበለዉ፡፡

የብሪክስ አባል አገራትን ከ5 ወደ 10 ከፍ ያደረጉት አገራት ኢትዮጵያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኢራን እና ግብጽ ናቸዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply