ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ ተቃወመችኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡አምባሳደር ምስጋኑ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/g0XFq7gJ-tQh4xINL0qzSNXZlPueGIPUB46EstCnJhbNLWWzdyRhrO0-JuA9ISfrysY0sSJ4piDVNM1wxVildz8KB9q15tBttNixaocNHiRYKnKJIlom12FVZW60qMUi6GARuykHZ2fx4PEilaGDzfoZolHJUdsX8EXWGbJtP8Zfsg9Ssw2QBtJiTRxUlTWPpxXndL5EbpzILeDkxjfMBYPPyg6s0xokYwaQVwqPKblXRmD_S6FQjHA7zz4Qnyw61Mz0vNags1rz9E39L0KeDchzp6Fnm997eWN_v7DepiRq3HLvmQ2zvaUyfmxZ16osYFJYyVaWTj89f6VZcqgpBA.jpg

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ ተቃወመች

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሊጉ መግለጫ፥ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለውታል፡፡

አክለው እንዳሉትም፥ ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት።

ሆኖም የአረብ ሊግ የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ እያስከበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የአረብ ሊግ ትናንት በግብጽ ካይሮ ባካሄደው የሚኒስትሮች ልዩ ስብሰባ ኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ እውቅና ያላገኘችው ሶማሌላንድ የተፈራረሙትን የወደብ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕግን በግልጽ የጣሰ ሲል አውግዟል፡፡

ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply