ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በቡና ምርት ላይ ያወጣውን ህግ ተግባራዊ ካላደረገረች 500 ሚሊዮን ብር ልታጣ ትችላለች ተባለ፡፡

ከወራቶች በፊት የአውሮፓ ህብረት ከጫካ ምንጠራ ጋር ተያይዞ የሚመረት የቡና ምርት ወደ አውሮፓ ሀገራት እንዳይገባ ያወጣውን ህግ ላኪ ሀገራት ተግባራዊ እንዲያደርጉት ትዛዝ አውጥቶ ነበር።

ወደ አውሮፓ ሀገራት በብዛት ቡና የምትልከው ኢትዮጵያ ህብረቱ ያወጣውን ህግ ተግባራዊ ካላደረገች 500 ሚሊዮን ብር ሊያሳጣት ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የአውሮፓ ህብረት አዲስ የቡና ግብይት ፖሊሲ ማውጣቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች አድርጋለች ብለዋል።

የቡና ግብይት መመርያ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ መጽደቁን ተከትሎ በተለይ ጀርመን እና ቤልጄም ያሉ ገዥዎች ውል ከመግባት እና ከመግዛት ይልቅ በመመሪያው ላይ ግልጽነት እስኪፈጠር በመጠበቃቸው ወደ አገራቱ ይላክ የነበረው ምርት ከ60 በመቶ በላይ መቀነሱን ተናግረዋል።

በዚህም ባለስልጣኑ ተጨማሪ ገበያ የማስፋት ስራ ሲሰራ እንደነበር እና ወደ ቻይና፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮርያ እና ሳውዲ አረቢያ የሚላከው ምርት መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ባወጣው ህግ መሰረት የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን የሚጎዱ ምርቶችን ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ገበያዎች እንዳይገቡ እና እንዳይሸጡ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

ከደን ምርቶች ጋር የተያያዙ ምርቶች በአውሮፓ የገበያ እድል እንዳያገኙ መከልከል እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ማበረታታት የህጉ ዋነኛ ዓላማ ነው ተብሏል።

ይህ ሕግ የጫካ ቡናዎችን ወደ አውሮፓ እና ሌሎች ዓለም ገበያ መዳረሻዎች የምትልከው ኢትዮጵያን እንደሚመለከት ስጋቶች ተነስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው ቡና ውስጥ 30 በመቶውን ወደ አውሮፓ ትልካለችም

ከአውሮፓ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱት ጀርመን እና ቤልጂየም መሆናቸው ባለስልጣን መስራቤቱ አስታውቋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply