ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተግባራዊ ያላደረገችው ፖለቲካውን የተቆጣጠረው አካል ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ስለፈለገ ነው፡፡ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት የካፒታል ገበያን ያልተገበረችው ፖለቲካውን የተቆጣጠ…

ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተግባራዊ ያላደረገችው ፖለቲካውን የተቆጣጠረው አካል ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ስለፈለገ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት የካፒታል ገበያን ያልተገበረችው ፖለቲካውን የተቆጣጠረው አካል በኢኮኖሚው የሚያገኝውን ጥቅም ላለማጣት በማሰቡ እንደነበር በስቶክ ማርኬት ዙሪያ ምሁራን የምክክር መድረክ ባደረጉበት ወቅት አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ዘመናት ኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ባለመተግበሯ የገንዘብ አቅርቦት መገደቡ በዚህም የተነሳ የግል ድርጅቶች በሚፈለገው መልኩ እንዳያድጉ መሰናክል እንደሆነባቸው የተገለጸው፡፡

ካፒታል ማርኬት ከሚያመጣቸው ልዩ ልዩ ጥቅሞች የግል የንግድ ድርጅቶችም ሆኑ የመንግስት ድርጅቶች ለሚያስፈልጋቸው የስራ ማስኬጃና የአቅም ግንባታ ማስፋፍያ አክሲዮን ወይም ቦንድ በመሸጥ ከማህበረሰቡ ገንዘብ የሚያገኙበት መንገድ ነው፡፡

ከዚህ በፊት የግልም ሆኑ የመንግስት ድርጅቶች ገንዘብ ሲያስፈልጋቸው ያገኙ የነበሩት ከባንኮች በብድር መልክ ብቻ እንደነበረ ሌላ አማራጭ የገንዘብ አቅርቦት መስመር እንዳልነበረ ይታወቃል፡፡

በውይይት መድረኩ የተገኙት የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት አቶ ተስፋይ ሀይለሚካኤል ስቶክ ማርኬት ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት የገንዘብ ገበያ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ምሁሩ ሀሳብ ከሆነ በዓለም 80 ትሪሊዮን ዶላር ሀብት በስቶክ ማርኬት ውስጥ ይንቀሳቀሳል እንደዚሁም በየዓመቱ 19 ትሪሊዮን ዶላር የአክስዮን ድርሻ ሽያጭና ግዥ ይፈጸማል ይላሉ፡፡

ነገር ግን ኢትዮጵያ ከዚህ የገንዘብ ሀብት መጠቀም እንዳልቻለች ነው አቶ ተስፋዬ የሚናገሩት፡፡

ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ የመንግስት የፖሊሲ መዋቅር እና ሀገሪቱ እየተመራችበት ያለው የኢኮኖሚ ስርአት ነው ይላሉ፡፡

ስቶክ ማርኬት በአገር ደረጃ የሚኖረውን የሸቀጥ ዋጋ ይቀንሳል እንዲቀንስ አስተዋጽኦ ከማድረጉም በላይ ፣ ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በዋጋ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚያስችላቸው ነው ምሁራን የሚናገሩት፡፡

ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ ፖለቲካው የተቆጣጠርው አካል ኢኮኖሚውንም መቆጣጠር ስለፈለገ ነው ይላሉ ምሁራኖቹ፡፡

ሔኖክ ወ/ ገብርኤል
ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply