ኢትዮጵያ የኬላ አስተዳደር ስርአቷ ከአለም የመጨረሻዎቹ ተርታ ላይ የሚያስቀምጣት ነው ተባለ።የሀገሪቷ የኬላ አስተዳደር ስርአት ጥብቅ ቁጥጥር ስለማይደረግበት ህገወጥ ሰዎች ያሻቸውን እያደረጉ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/TnA2wWoceUfY6dQJy39UWX3MhVP6jCx-DPe7HukfLio3Z_-V-1aBYVmvAJiHia4TFB2qdCwbA__PGAscXBX7DHQu8V4H7Zl6TjTK_HIyOldCmuCmcoMZ2VhRgdS3yZTcfVmnKh4h0fh_Py2FCuwUo8Rf4oVtsQUCIaaTtQRV8n2ocsRjQTA88Y3786528eprRrvRaJpYsHH4z6LG5m5XJzFU7x7YvkXHZpRjROUMqFW9ONmGRF5iTGpYLrs1JSMxJotHMH8mkcjW05FA86SYqncoVukl2gjgny6Nm_5iTcsLBSMvUr0IwWroZCL8SfeBGR_tVutSeyq_Khi1ew3-tA.jpg

ኢትዮጵያ የኬላ አስተዳደር ስርአቷ ከአለም የመጨረሻዎቹ ተርታ ላይ የሚያስቀምጣት ነው ተባለ።

የሀገሪቷ የኬላ አስተዳደር ስርአት ጥብቅ ቁጥጥር ስለማይደረግበት ህገወጥ ሰዎች ያሻቸውን እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን አገልግሎት ምክትል ዳሬክተር አቶ ጎሳ ተስፋዬ እንደተናገሩት የኬላ አስተዳደራችን ደካማ በመሆኑ በርካታ ችግሮች እያስተናገደን ነው የቆየነው ብለዋል።

የህ ሀገሪቷ ለዘርፉ ትኩረት አለመስጠቷን  የሚያሳይ ነውም ብለዋል።

ለኬላ አስተዳደር የሚመደቡ ሰራተኞች በተመለከተም አቶ ጎሳ እንደተናገሩት ከዋናው መስራቤት በሌብነት እና በብልሹ አሰራሮች የተጠረጠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ የኬላ አስተዳደር ስርአት ጋር በተያያዘም ሀገረ መንግስታቸው ተዳክሟል የሚባሉ እንደ ጎረቤት ሀገር ሱማሊያ የኬላ አስተዳደር እንደሚሻል ምክትል ዳሬክተሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የኬላ አስተዳደር ስርአት ደካማ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የውጭ ሀገር ዜጎች ሳይቀሩ የተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ እንደቆዩም አቶ ጎሳ ተናግረዋል።

በመሆኑም ይህ ጉዳይ ዛሬ ነገ ሳይባል ትኩረት ተሰቶት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢሚግሬሽን አገልግሎት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ከአሰራሮቹ ጋር በተያያዘ በርካታ ክፍተቶች እንዳሉ አስታውቆ በአዲስ አሰራር ችግሮቹን ለመቅረፍ የሚያስችል ስልት መንደፉን ገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply