ኢትዮጵያ የክትባት መድሃኒቶችን በሃገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል የመጀመሪያውን ፋብሪካ ልትገነባ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በርካታ የክትባት መድሃኒቶችን ከውጭ በማስመጣትና በመጠቀም የምትታወቀው ሃገራችን አሁን ላይ የውስጥ አቅሟን ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በዛሬው እለትም የጤና ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ የክትባት መድሀኒቶችን ማምረት የሚያስችል የመጀመሪያውን ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ በቂልንጦ ኢንዱስተሪ ፓርክ ግቢ ውስጥ እንደሚያስቀምጥ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ስነ-ስርዓቱ ላይም የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የአለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች የስራ ሀላፊዎች እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply