ኢትዮጵያ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን “ዛቻ” ተቃወመች

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-498d-08db27247f4f_tv_w800_h450.jpg

ከታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ “ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ህገወጥ የማስፈራራት ዘመቻ ቀጥላለች” ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቃውሞ አሰምቷል።

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ “አዲስ አበባ በአባይ ተፋሰስ የግርጌ ሃገሮች ላይ ጉልህ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረግ ካልቻለች ግብፅ የህዝቧን ጥቅም ለማስጠበቅ እርምጃ ትወስዳለች” ማለታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ “የሹክሪ ዛቻ ዓለምአቀፍ ህግን ባፈጠጠ ሁኔታ የሚፃረር የማስፈራራት አድራጎት ነው” ብሎታል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መልዕክቱን ያስተላለፉት እዚያው ጉብኝት ላይ ካሉት የኬንያ አቻቸው አልፍሬድ ሙቱአ ጋር ሆነው ካይሮ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply