ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካን መርዝነት የተረዳ መሪ አላት ወይ? እንደርሱ ችግሩን የተረዱ የመንግስት ባለስልጣናትስ አሉ ወይ? መልሱ አዎን! ነው። መሪዎቿ ከሁሉ በፊት የሰው ህይወት ለመታደግ መንቀሳቀስ አልነበረባቸውም ወይ? አሁንም መልሱ አዎን! ነበረባቸው ነው።ኢትዮጵያውያን! ወቅታዊውን ችግር በቅንጥብጣቢ ጊዜያዊ መፍትሔ አንፈታውም።

ለውስጣዊ የጸጥታ ችግሮቻችን መፍትሔነት ሦስቱ መፈታት ያለባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች።==========ጉዳያችን ምጥን==========በማንነት ጥቃት ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ፣ሲታሰሩና ሲሰደዱ ዓመታት ተቆጠሩ።በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት እጅግ ጽንፈኛ እና ዘረኛ አደረጃጀት የነበራቸው እንደ ኦነግ ያሉ አደረጃጀቶች ወደ ሃገር ውስጥ ገብተው በፌድራል እና በተለየ በኦሮምያ ክልል ከልዩ ኃይል አባልና አመራር እስከ የክልሉ ምክርቤት ድረስ ገብተዋል። ይሄው ኃይል የነበረውን የኢትዮጵያን የመጥላት እና በአማራ ላይ የተተረከለትን ትርክት እና እራሱ የፈጠራቸውን ፈጠራዎች ይዞ ትውልድ በክሏል። በወለጋ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ዘርን መሰረት

Source: Link to the Post

Leave a Reply