
ኢትዮጵያ የጮቄ ተራራ ኢኮ ቱሪዝም ልማት የቱሪዝም መንደር ያሸነፈውን የዓለም ድንቅ ቱሪዝም መንደር ሽልማት ተቀብላለች። መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በጮቄ ተራራ የሚገኘዉ የሙሉ ኢኮሎጂ የኢኮ ቱሪዝም ልማት መንደር የዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደር ሽልማትን ያሸነፈ በመሆኑ ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ሽልማቱን መቀበሏ ታውቋል። ድርጅቱ በአማራ ክልል ጎጃም የሚገኘውን የጮቄ ተራራ ኢኮ ቱሪዝም ልማት የዓለም ድንቅ ቱሪዝም መንደር ውድድር አሸናፊ አድርጎ መርጧል። በእለቱም ከ50 በላይ ሃገራት ከ100 በላይ የቱሪዝም መዳረሻዎች ጋር ከተወዳደረ በኋላ ነው አሸናፊነቱ የተረጋገጠው። ሽልማቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ከጮቄ ሙሉ ኢኮ ሎጅ ተወካዮች ጋር በመሆን በሳውዲ አረቢያ አሉላ ከተማ ከድርጅቱ ሴክሬታሪ ጀኔራል እጅ ተቀብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ሴክሬታሪ ጀኔራል የኢትዮጵያው ጮቄ ሙሉ ኢኮ ሎጅ ከ100 በላይ የቱሪዝም መዳረሻዎች ጋር ተወዳድሮ የሸነፈው ማኅበረሰቡን በማሳተፍ እና በዘላቂ ልማትነቱ በልጦ በመገኜቱ ሊመረጥ መቻሉ ተገልጿል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post