You are currently viewing ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታሪክ እንጂ የተሸነፈችበት ታሪክ ኖሮ አያውቅም”ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተናዉ ታህሳስ 10/2014/አሻራ ሚዲያ / ባለሀብቱ አቶ ወርቁ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸዉ እንደገ…

ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታሪክ እንጂ የተሸነፈችበት ታሪክ ኖሮ አያውቅም”ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተናዉ ታህሳስ 10/2014/አሻራ ሚዲያ / ባለሀብቱ አቶ ወርቁ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸዉ እንደገ…

ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታሪክ እንጂ የተሸነፈችበት ታሪክ ኖሮ አያውቅም”ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተናዉ ታህሳስ 10/2014/አሻራ ሚዲያ / ባለሀብቱ አቶ ወርቁ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸዉ እንደገለፀቱት የሀገሬ ህዝብ ሆይ ድል መምታት የእኛ እንደሆነ ሁሌም ነግሬህ ነበር አይደል ይሄው ኢትዮጵያ ባፈራቻቸው በቁርጥ ቀን ልጆቿ ጠላትን እያሳፈርን ተደጋጋሚ የድል ምዕራፎችን እያለፍን እንገኛለን። አሁን የመጨረሻው ምዕራፍ ሊጠናቀቅ በአማራና በአፋር መሬት ለይ ሲፈነጭ የነበረው ጠላት ሙሉ ለሙሉ ከአማራ እና ከአፋር መሬት ለይ ተለቅሞ ድል ተደርጎና ተደምስሶ ወጥቷልይህን ጀግንነት የፈጸምክ የሀገሬ ህዝብ በሙሉ እንኳን ደስ አለህ ብለዋል ። የተከበራችሁ የወልዲያ እና የአካባቢው ህዝቦች ሆይ እንኳንም ደስ አላችሁ በቅርቡ እኔና እኔን መሠል ጓደኞቼ አጠገባችሁ በመገኘት ካላችሁበት ችግር ለማውጣት ከችግራችሁ ጎን ሆነን ችግራችሁን ለመፍታት በህብረት መጥተን እንጎበኛችኋለን የቻልነውን ሁሉም እናደርጋለን። እንደዚህ አንድ ከሆንንና ከተባበርን ደግሞ የታፈነውን የትግራይን ህዝብ ነጻ አውጥተን ከወንድሞቹ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብሮ የሚኖርበትን ስርአት የምንዘረጋበትና ጁንታውን እስከመጨራሻው የምናስወግድበት ምዕራፍ ይሆናል ያሉ ሲሆን። የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ልጆችህ አላማ ለሌለው ጦርነት እና የስግብግቡን የጁንታውን የስልጣን ጥማት ለማስጠበቅ ብቻ በሺህ የሚቆጠሩ ጨቅላና ሮጠው ያልጠገቡ ልጆችህ በወጡበት ቀርተዋል። ይህ ጦርነት የማይታሰብና የማይታለም ከ115 ሚሊየን ህዝብ በላይ አሸንፋለሁ ብሎ የተነሳው ትዕቢተኛው ብሎም የውሸት ኢንፎርሜሽን ለትግራይ ህዝብ እየሰጠ ከሌላው ብሄር ብሄረሰቦች ጋር የሚያባላውን የህውሀትን አመለካከት ተከትለው አላግባብ ወጥተው ሳይመለሱ የቀሩ የልጆችህ ጉዳይ ሊያምህ ይገባል። ስለሆነም ይሄ ሁሉ ሆኖ ያለምንም ውጤት በጉራ ደረቱን እንደነፋ ጁንታው እዚህ ደረጃ ለይ ደርሶ የሽንፈት ካባውን ተጎናጽፏል። የጁንታው ደጋፊ ያልሆናችሁ የታፈናችሁና ደጋፊ የሆናችሁ የትግራይ ተወላጅ የሆናችሁ በሙሉ የማስተላልፍልህ መልዕክት ከእዚህ በኋላ ከመሀል አገር ሌላ ሰው መጥቶ ነጻነትህን እስከሚያስጠብቅልህ ከምትጠብቅ ዛሬውኑ ይበቃኛል ብለህ ከእዚህ በፊት የተፈጸመብህን ነገር ሁሉ ተረድተህ ጁንታውን እያነቅክ ለመንግስት በማስረከብ እና እንዲሁም ከአማራ ክልል ተዘርፈው የሄዱትን አንዲትም ማንኪያ ሳትቀር የአማራን ህዝብ ንብረት እንዲመለሱ እንድታደርግና ኢትዮጵያዊ ጨዋነትህን እንድታሳይ ላሳስብህ እወዳለሁ። የትግራይ ህዝብ አሁንም ደግሜ ላሳስብህ የምፈልገው እስካሁን በውሸት ምላሱ ሲያታልልህና ሲዋሽህ የነበረውን ጁንታና ባንዳ ውሸታም መሆኑን ተረድተህ በራስህ ዳኝነትና ፍርድ ሰጪነት እያነክ በቁጥጥር ስር አውለህ ይበቃናል አውቀናችኋል በማለት ተጋድሎ በመፈጸም ኢትዮጵያዊነትህን አጠናክረህ ከውንድሞችህ ጋር እንድትኖር ደግሜ ደጋግሜ አደራ እላለሁ። ሌላው በመላው አለም የምትገኙ ዲያስፖራዎች ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ በገባችበት ጊዜና በጁንታ በገጠማት ጀኖሳይድ የኢትዮጵያና የአማራ ክልል መብት እንዲከበር ሌሊትና ቀን ጥረት ያደረጋችሁ ዲያስፖራዎች በሙሉ እጅግ በጣም በጣም የምናመሠግናችሁ መሆኑንና ታሪክ የማይረሳው ጀብድ የፈጸማችሁ መሆኑን ደግሜ ልነግራችሁ ወደድኩ። በእዚህ አለም ጦርነት በክላሽ ሳይሆን በፖለቲካ የበላይነት እና እንዲሁም በሀቅ የበላይነት ተመስርቶ ለአለም በማሳወቅና በማሳየት ለይ ብቻ የተመሠረተ ሂደትን በመገንዘብ በፍጥነት ወደ እንቅስቃሴው በመግባት ይሄን ሁሉ ላደረጋችሁት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እግዚያብሔር ውለታችሁን ይክፈላችሁ። ኢትዮጵያም ውለታችሁን ትከፍላችኋለች ። ላደረጋችችሁ ነገር ሁሉ በእኔ በኩል በጣም በጣም አመሠግናለሁ ብለዋል። “

Source: Link to the Post

Leave a Reply