የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት በየነ መረብን (online petition) በመጠቀም የተቃወሞ ፊርማን መሰብሰብ የሚያስችል አዲስ አሰራር ይዞ ቀርቧል።
ጽህፈት ቤቱ ባለፈው ሳምንት ”ግብፆች ግድቡን ያፈነዱታል” በማለት ዶናልድ ትራምፕ የተናገሩትን ግዴለሽ ንግግር ተከትሎ፣ ሁለት አይነት የበየነ መረብ ፊርማ ማሰባሰቢያ ድረገፆችን አዘጋጅቶ የፊርማ ማሰባሰብ ስነስርአተን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።
የመጀመሪያው ”we the people” የሚል ድረ ገጽ ሲሆን፣ አቤቱታን ማሰሚያ መድረክ አማካኝነት የአሜሪካው ዋይት ሀውስ ላይ የተኮረ ነው ተብሏል። ሁለተኛው ደግሞ ”change.org” የሚል ድረ ገጽ ሆኖ፣ አለም አቀፋዊ ማህበረሰቡን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።
የፊርማ ማሰባሰቢያ ስነስርዓቱን ያሰጀመሩትና የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አረጋዊ በርሄ እንዳሉት፣ ፅህፈት ቤታቸው ላለፉት አመታት በተቀናጀ መልኩ ለግድባችን ግንባታ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በማሰባሰብ በቁርጠኝነት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው፣
በመሆኑም ”ሁሉም ኢትዮጵያን፣ ትውለደ ኢትዮጵያዊንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ ይህንን የበየነ መረብ የፊርማ ማሳሰብያዎች በመጠቀም፣ ፊርማቸውን እንዲኖሩና በፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ሳቢያ የተሰማቸውን ንዴትና ተቃውሞ እንዲገልጹም” ጠይቀዋል።
በተላይ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን እነዚህን ድረገፆች ለሁሉም ሰዎች በሙሉ ተደራሽ እንዲደርጉ ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬ ከ150 የሚበልጡ ሰዎች ይተቃውሞ ፊርማቸውን በመፈረም የትራምፕን አስተያየት መቃወማቸውን የገለፁ ሲሆን በ 1 ሳምት ውስጥ ብቻ 100 ሺህ ሰዎች ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጅብሪል ሙሀመድ
ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም
Source: Link to the Post
I condemned donald trump speech on GERD .stop
Stop trump!!!
Us president Egyptians can blow up Largest ethiopian dam . Thus is not expected from trump
Ethiopia is sovereign country
Has legal rights to built dam on his resources
Which is questions of mind
We strictly condemned his speeches