ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የሚያደርጉትን 4ኛውን ዙር የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄዱ ነው። የአሁኑ ድርድር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/YCrWz-AS-UdmiI7dBaZEEaeSjmln_fqD8XbD3sHhwyxkg6m_VyhRrjZkeNTRkCGFmVjFAqRVFAHyg_LSfMJ_mBM_4pbR4VVGjMAzzS_14DJVRCRs7aF51MnKj6PMVeosl88Am6I8LOyDoqdwvyYyklXeZ6tnJsxs1lmpjgr3-UoODX_y51Yk0qEYjlPSDq7h0FP4aXQ-02Nzj49dnVhPEEKK3zF8KAcIOkL-K6eY72I9aRd5PH-fohNlMl_zHMJfPh-_VePzSTcScaQ5yt6IJXGwM40d0PW8Y_r_Typ1Jl4zGP4hBwNvn5JXuG6tgw1L98ie6NhduNVK1PMBWq4YNw.jpg

ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የሚያደርጉትን 4ኛውን ዙር የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄዱ ነው።

የአሁኑ ድርድር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እና የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግድቡ ሙሌት እና አስተዳደር ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን እና ደንቦችን ለማጠናቀቅ የተፋጠነ ድርድር ለመጀመር የጋራ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው።

በሚንስትሮች ደረጃ እየተደረገ ያለው ድርድሩ ቀደም ሲል ሲደረጉ የነበሩ ድርድሮችን ማስቀጠል ፣ እንዲሁም ትናንት ከዚህ ስብሰባ አስቀድሞ በቴክኒክ ባለሞያዎች ደረጃ የተካሄዱ ንግግሮችን አጠናክሮ ያስኬዳል ነው የተባለው።

ኢትዮጵያ በጎርጎርሳውያኑ 2015 በወጣው የታላቁ ህዳሴ ግድብ መርሆች እንደምትመራ እና በመርህ ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ የአባይ ወንዝ አጠቃቀም ያላትን አቋም እንደምታጸና ኢትዮጵያን ወክለው በድርድሩ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በ X ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የአፍሪቃ ግዙፍ ግድብ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር ላይ ሶስቱ ሃገራት በተደጋጋሚ ሲያደርጓቸው የነበሩ ድርድሮች ከአንዳች ገዥ ስምምነት ሳይደርሱ ዘልቀዋል።

ታህሳስ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply