ኢትዮጵያ 13 ሚሊዮን ዩሮ ግምታዊ ዋጋ ያላቸዉ የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁሶች ከኢጋድ ድጋፍ ሊደረግላት ነዉ፡፡የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት /ኢጋድ/ ግምታቸዉ 13 ሚሊዮን ዩሮ…

ኢትዮጵያ 13 ሚሊዮን ዩሮ ግምታዊ ዋጋ ያላቸዉ የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁሶች ከኢጋድ ድጋፍ ሊደረግላት ነዉ፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት /ኢጋድ/ ግምታቸዉ 13 ሚሊዮን ዩሮ የሆነ የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡

የኢትጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንሲስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት / IGAD/ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚዉሉ የህክምና መሳሪዎችን በነገዉ እለት ለኢትዮጵያ መንግስት ያስረክባል ብሏል፡፡

ድጋፉን የሚያደርጉት የበየነ መንግስታቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንደሆኑም ኢንስቲትዩቱ አስታዉቋል፡፡

ድጋፉ የተለያዩ የኮሮና ቫይረስ መከላከያና እና የህክምና መሳሪያዎችን ያካተተ ሲሆን ዋጋቸዉም 13 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት በቀጣይ ለኢትዮጵያ በሚያደርገዉ ድጋፍ ዙሪያም በነገዉ እለት ዉይይት እንደሚደረግም ሰምተናል፡፡

በነገዉ እለት እንደሚከናወን በተገለጸዉ በዚህ መርሃ-ግብር የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የኢጋድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ርክክብ እንደሚያደርጉም ታዉቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply