ኢትዮ ልዩ!ድንቃድንቅ መረጃዎችን እንሆ!1፤ድብብቆሽ እየተጫወተ ሳለ ድንገት እራሱን ሌላ ሃገር ያገኘው ልጅ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡የባንግላዲሽ ዜግነት ያለው ይህ ልጅ ድብብቆሽ በመጫወት ላይ…

ኢትዮ ልዩ!

ድንቃድንቅ መረጃዎችን እንሆ!

1፤ድብብቆሽ እየተጫወተ ሳለ ድንገት እራሱን ሌላ ሃገር ያገኘው ልጅ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የባንግላዲሽ ዜግነት ያለው ይህ ልጅ ድብብቆሽ በመጫወት ላይ ሳለ ከጓደኞቹ ለመደበቅ የገባበት ኮንቴይነር በመርከብ ወደ ማሌዢያ ይዞት አምርቷል፡፡

ከባንግላዲሽ ወደ ማሌዢያ በርካታ ኮንቴይነሮችን ይዞ ባቀናው መርከብ ውስጥ የነበሩ ሰራተኞች ልጁን በማየታቸው እጅጉን መደናገጣቸው ነው የተገለጸው፡፡

ድብብቆሽ እተጫወተ እንደነበር የሚያስታውሰው ልጅ “ፏይም” ለስድስት ቀናት ያለምንም ምግብ ኮንቴይነር ውስጥ ቆይቶ በህይወት መትረፉም ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

ህጻኑ ልጅ የአካባቢውን ቋንቋ ተናጋሪ ባለመሆኑ በወቅቱ የአከባቢው ባለስልጣናት ምንም አይነት መረጃ ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ልጁ በባንግላዲሽ ከጓደኞቹ ጋር ድብብቆሽ እየተጫወተ እንደነበር እና ኮንቴይነሩን መደበቂያ አድርጎ በተደበቀበት ሰዓት ወደ ማሌዢያ ሊመጣ መቻሉን ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

ልጁም ከባንግላዲሽ ወደ ማሊዢያ በሚጓጓዘው መርከብ ውስጥ ሄዶ እራሱን በአዲስ ቦታ በማግኘቱ መደናገጡን እና ሲያለቅስ እንደነበር የመርከቡ ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

በኋለም ልጅ ፏይም ወደ ሆስፒታል ተወስዶ አስፈላጊው ድጋፍ እንደተደረገለት ኦዲት ሴንተራል በመረጃው አትቷል፡፡

በባንግላዲሽ እና ማሌዢያ መካከል የ2ሺህ ማይል እርቀት እንዳለም መረጃው አመላክቷል፡፡(በመሳይ ገ/መድህን)

2፤ከመኝታ በፊት የወተት ተዋጽኦዎችን ለሚመገቡ ሰዎች 53 ሺህ ብር እከፍላለሁ ያለው ድርጅት ትኩረት ስቧል፡፡

ስሊፕ ጆኪ /Sleep Junkie/ የተባለው ይህ ድርጅት በተለያዩ የህክምናና የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን ሰዎች እንዴት ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ይችላሉ? በሚሉና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ የማማከር ስራን ይሰራል፡፡

በአሜሪካ በብዙዎች ዘንድ ከመኝታ በፊት አይብና ሌሎችንም የወተት ተዋጽኦዎች መመገብ ለቅዠት ይዳርጋል፤ ሰዎች ጥሩ እንቅልፍ እንዳያገኙም ያደርጋል የሚል ግምት እንዳለ ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

በመሆኑም ይህ ጉዳይ ምን ያህል እውነትነት አለው? የሚለውን ለማረጋገጥ ወደ መኝታ ከማምራታቸው በፊት የወተት ተዋጽኦዎችን የሚወስዱ 5 ሰዎች ያስፈልጉኛል ብሏል፡፡

ጥናቱ ከየካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለ3 ወራት የሚቆይ ሲሆን የወተት ተዋጽኦዎችን ወስደው የሚተኙና በጥናቱ የተካተቱ ሰዎች ስለ አገኙት እንቅልፍ ጥሩነት እና በቀጣዩ ቀን የነበራቸውን ንቃት በተመለከተ መረጃዎችን እንዲሰጡ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ሰዎቹ ለዚህ ስራቸው አንድ ሺህ ዶላር ወይም 53 ሺህ 430 ብር ክፍያ ያገኛሉ ብሏል፡፡

ድርጅቱ በሶስተኛው ወር መጨረሻ ላይ በሰዎች ላይ ያለው አስተሳሰብ ትክክል ወይም የተሳሳተ አመለካከት መሆኑን የሚያሳይ የጥናት ውጤት ይዤ እመጣለሁ ማለቱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡(በሙሉቀን አሰፋ)

3፤ለቀድሞ ፍቅረኛዋ ከ1 ሺህ በላይ የጽሁፍ መልዕክቶችን የላከችው እንስት ክስ ቀረበባት፡፡

የ28 አመቷ እንግሊዛዊት ሚሼል ፌልቶን፣ ሃርሊ ከተባለ ወጣት ጋር የነበራት የፍቅር ግንኙነት ባላሰበችው ሁኔታ መለያየት ላይ ደረሰ፡፡

ፌልቶን ይህን ግንኙነት ለመመለስ በቀን 150 የጽሁፍ መልዕክቶችን በአጠቃላይ 1 ሺህ የጽሁፍ መልዕክቶችን ልካለች፡፡
ጉዳዩ ወደ ክስ አምርቷል፡፡

ሃርሊ ተነጋግረን በዘጋነው ጉዳይ ነጻነቴን ተነፍጊያለሁ ባይ ሲሆን ፌልቶን ደግሞ ለጋራ ህይወታችን ስል ያደረኩት ነው በሚል እየተከራከሩ ነው ሲል ሚረር ነው ያስነበበው፡፡(በአቤል ደጀኔ)

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply