ድንቃድንቅ መረጃዎች ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
1፤ሩሲያዊው የአይ ቲ ባለሙያ ጦርነትን ሽሽት ለ4 ወራት በቀዝቃዛው ደን ውስጥ ተደብቆ ተገኘ፡፡
ግለሰቡ የፕሬዝዳንት ፑቲንን ጥሪ ላለመቀበልና ከዩክሬን ጋር የሚደረገውን ጦርነት በመቃወም ለ4ወራት ያህል ጫካ ውስጥ ተደብቆ ኑሮውን ማድረጉ ግርምትን ፈጥሯል፡፡
አደም ወይም አሊያስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ይህ የአይ ቲ ባለሙያ ግለሰብ፣ ሀገሩ ከዩክሬን ጋር ያለውን ጦርነት ከመጀመሪያው ጀምሮ በመቃወም የሚታወቅ ሲሆን፣ ቤቱ ደጃፍ ላይ ጦርነቱን የሚያወግዝ ባነር በመለጠፉ ለ 2 ሳምንት ታስሮ መፍታቱ ነው የተገለፀው፡፡
ታድያ ሀገሩ ለ300ሺህ የሃገሪቱ ዜጎች የክተት አዋጅ ስታውጅ፣ ይህ የአይ ቲ ባለሙያ ይህንን አዋጅ ሽሽት ወደ ጫካ በመሄድ ለ4ወራት ኑሮውን አድርጎ መቆየቱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፤
(በአቤል ደጀኔ)
2፤ወደ ወጣትነቱ ለመመሰለስ በየዓመቱ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣው ግለሰብ ጉዳይ፡-
የ45 አመቱ አሜሪካዊ ቴክ-ሞጉል ወደ ቀድሞ ወጣትነቱ ለመመለስ በዓመት 2 ሚሊዮን ዶላር ወይም 106 ሚሊዮን ብር አካባቢ ያወጣል ሲል ዩ ፒ አይ ዶት ኮም አስነብቧል፡፡
ብራያን ጆንሰን የተባለ ግለሰብ ባገኘው አዲስ ቴክኖሎጂ አማካይነት የ45 አመቱ ቴክ ሞጉል ጤንነቱ እና ቆዳውን በማይጎዳ ሁኔታ በቴክኖሎጂው ወደ ወጣትነቱ ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
ግለሰቡ በአመት 2 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣበት ይህ ቴክኖሎጂ የ37 አመት ሰው ልብ፣ የ28 አመት ቆዳ እና የ18 አመት ታዳጊ የሳንባ አቅም እና የአካል ብቃት ደረጃ እንዳለው ያስመስላል ተብሏል፡፡
ቴክ ሞጉል ይህንን የሰውነት ገጽታውን አስቀጥሎ ለመሄድ 30 ሃኪሞችን ያካተተ ቡድን እንዳለውም ተነግሯል፡፡
እነዚህም ቡድኖች የሰውነት ተግባራቱን የሚከታተሉ እና በእያንዳንዱ የአካል ክፍሎቹ ውስጥ ያለውን የእርጅና ሂደት የሚያስተካክሉ እንደሆኑም ተገልጿል፡፡
ታዲያ የዚህን ሰው ሰውነት እንዳያረጅ ለማድረግ የቴክኖሎጂው ባለቤት የሆነው ጆንሰንን ጨምሮ ቡድኖቹ በእርጅና እና ረጅም ዕድሜ ላይ ባሉ ሳይንሳዊ ጽሑፎች ተጠምደው እንደሚውሉ ታውቋል፤
እስካሁን ባደረጉት ምርምር ይህ ግለሰብ ሳያረጅ እንዲቆይ የሚያደርግ ተስፋ ሰጪ ውጤት እንዳገኙ መረጃው አመላክቷል፡፡
ግለሰቡ የሚያገኘው ህክምና በቀን ሰባት አይነት ቅባቶችን መቀባት እና ሳምንታዊ የሌዘር ቴራፒ ምርመራን በማድረግ ሲሆን በቆዳው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስተካክልለታል ተብሏል፤
(በመሳይ ገ/መድህን)
3፤በቤልጀም የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ የሰው ልጅ ጸጉርን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥረት እያደረገች ነው ተባለ፡፡
የሰው ልጅ ጸጉርን በመጠቀምም ምንጣፍና ቦርሳን እየሰራች ነው ተብሏል፡፡
ለመልሶ ጥቅም የሚውለው ፀጉር በተዘጋጀለት ማሽን ውስጥ ከገባ በኃላ በፀጉር ውስጥ ያለውን ቅባት እና ሌሎች ሀይድሮ ካርቦኖች ከባቢን የሚበክሉትን ካስወገደ በኃላ ከፀጉር ቦርሳና ምንጣፍ መስራት ተችሏል ነው የተባለው፡፡
የፕሮጀክቱ ተባባሪ አዘጋጅ የሆኑት ፓትሪክ ጄንሰን እንደሚሉት፣ አንድ ምንጣፍ ለመስራት 1ኪሎ ግራም ፀጉር እንደሚጠቀሙና ይህም ከ7 አስከ 8 ሊትር ቅባትና ሀይደሮ ካርቦን ማሽኑ በመምጠጥና በማስወገድ ብክለት ለመቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post