“ኢትዮ ቲክቶክ” የተሰኘ አገርኛ የቪዲዮ ምስል መተግበሪያ ይፉ ተደረገ።ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎችን በቀላሉ ማስተላለፍ የሚቻልበት፣ ወጣቱ የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግና ምርት…

“ኢትዮ ቲክቶክ” የተሰኘ አገርኛ የቪዲዮ ምስል መተግበሪያ ይፉ ተደረገ።

ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎችን በቀላሉ ማስተላለፍ የሚቻልበት፣ ወጣቱ የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግና ምርትና አገልግሎትን ለብዙሃን ማድረስ ያስችላል የተባለለት “ኢትዮ ቲክቶክ” የተሰኘ አገርኛ የቪዲዮ መተግበሪያ ይፉ ተደረጓል።

መተግበሪያው ይፉ ያደረጉት በቴክኖሎጂና የፈጠራ ሥራዎች ላይ ተሰማርቶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው ኢንፍራቴክ የሶፍዌር ሰርቪሶች ሀ/የተ/የግል ማህበር እና የትም ትሬዲንግና ዴሊቨሪ ሲሆኑ፤ ተቋማቱ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

በ”ኢትዮ ቲክቶክ” ላይ የሚለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች አገራዊ ይዘት እንዲኖራቸው እንደሚደረግና ይህንንም የሚቆጣጠር ሥርአት መዘርጋቱ የገለጹት ኢንፍራቴክ የሶፍትዌር ሰርቪስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀዳማዊ ሙሉአለም የተለያዩ ተቋማት እና ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን በመተግበሪዊ በመጠቀም ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የየትም ትሬዲንግና ዴሊቨሪ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ መንሱር ጀማል በበኩላቸው፤ መተግበሪያው በአገር ውስጥ ቋንቋዎች የሚሰራ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ የተለያዩ ኦንላይን ጨዋታዎች ወደ መተግበሪያው እንደሚጨመሩ አስረድተዋል።

መተግበሪያው ለተጠቃሚዎች በአንድ ላይክ (like) አንድ የኢትዮጵያ ብር እንደሚከፍል የተገለጸም ሲሆን፤ ነገር ግን ለክፍያ ስርዓቱ አመቺነት ሲባል የተጠቃሚው የቲክቶክ ሥም (user name) እና የባንክ አካውንቱ ሥም ተመሳሳይ ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል።

ኢትዮ ቲክቶክ ለበርካታ ወጣቶቾ የስራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ  የሀገራችንን ሁኔታ ያገነዘበ በመሆኑ እሴቶቻችንን ከማስጠበቅ አንፃር ይሰራል ብለዋል የኢንፍራቴክ ሶፍትዌር ሰርቪስ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ቀዳማዊ ሙሉአለም።

በየትም ዲሊቨር ሶፍትዌር ባለቤት መንሱር ጀማል እና በኢንፍራቴክ ሶፍትዌር ሰርቪስስ መካከል የፊርማ ስነ ስርዓት በማካሄድ አብረዉ ለመስራት ተስማምተዋል።

በአቤሌ ደጀኔ

Source: Link to the Post

Leave a Reply