ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ 42.9 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ አለ።

ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ 6 ወር ጊዜ ውስጥ 42.9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።

ኩባንያው የትርፍ መጠኔም 11.5 ቢሊየን ብር ሆኗል ነው ያለው።

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በገቢም ሆነ በትርፍ ጭማሪ መታየቱን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ገልጸዋል።

በዚህም የኩባንያው ገቢ በብር 8.86 ቢሊየን ወይም የ26በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

ለተገኘው ገቢ ከፍተኛ ድርሻ የነበረው የድምፅ አገልግሎት ሲሆን ዳታና ኢንተርኔት እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ገቢ እና ሌሎች አገልግሎቶችም አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ኩባንያው ያገኘው ትርፍ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ14 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

ይህም የኩባንያውን የትርፋማነት መጠን 26 በመቶ አድርሶታል ነው የተባለው።

የኩባንያው ደንበኞች በዚህ 6 ወር ጊዜ ውስጥ ከ74 ሚሊየን በላይ መድረሳቸውም ተገልጿል።

የቴሌብር ደንበኞች ደግሞ 41 ሚሊየን ደርሰዋል የተባለ ሲሆን፤ በዚህ 910 ቢሊየን ብር ዝውውር ተካሂዷል።

ኩባንያው በግማሽ ዓመቱ አጋጥመውኛል ካላቸው ችግሮች መካከል በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ባጋጠሙ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት የአገልግሎት መቋረጥ፣ በኔትዎርክ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ፣ ስርቆት፣ የቴሌኮም ማጭበርበር፣ የግንባታ ስራ ግብዓቶች ዕጥረት፣ የገበያ አለመረጋጋት እና የሃይል አቅርቦት መቆራረጥ ናቸው።

እስከዳር ግርማ
ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply