ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት ደርሶበታል የተባለው ኪሳራ አይመለከተኝም አለ።

ኩባንያው በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በተነሱ ግጭቶች ምክንያት በተከሰተው የኢንተርኔት መቋረጥ አጥቷል የተባለው ገንዘብ ትክክለኛ ቁጥር አይደለም ብሏል።

ኩባንያው በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት 1.5 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል ሲል አንድ ዓለም ዓቀፍ ተቋም ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት የገቢ መቀነስ ያለ ቢሆንም በፍጹም ግን ኩባንያው የዚህን ያህል ገንዘብ አላጣም ብለዋል።

የወጣው ሪፖርትም ቀጥታ የሚመለከተን አይደለም፤ የገቢ ክፍተትም አልተፈጠረም ነው ያሉት።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በተዘጉ ኔትወርኮች ምክንያት ገቢ ይቀንሳል እንጂ ይህን ያህል የገንዘብ መጠን አይታጣም ሲሉ ገልፀዋል።

ተቋሙ ይህን ሪፖርት ሲያወጣ የኢንተርኔት መዘጋቱ በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን ተያያዥ የሆነ ጉዳት አብሮ የሚያሰላበት አግባብ ይኖረዋል እንጂ ኩባንያው በቀጥታ ይህን ያህል ገንዘብ አላጣም ብለዋል።

በአለም ዓቀፍ ደረጃ የወጣውንም ሪፖርት የምንቀበለው አይደለም ብለዋል።

እስከዳር ግርማ
ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply