ኢትዮ ቴሌኮም በከተማዋ የመልሶ ማልማት ስራዎች ሳቢያ የኔትዎርክ መቆራረጥ ሊያጋጥም ይችላል ሲል አሳስቧል

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ባለው የመንገድ ኮሪደር ልማት እና ሌሎች የመልሶ ማልማት ሥራዎች ምክንያት የፋይበር፣ የታወር እና የተለያዩ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች እየተነሱ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በዚህም የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ግንባታ በማከናወን አገልግሎት ለማስቀጠል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጽ፤ የኔትዎርክ መቆራረጥ ወይም የአገልግሎት ጥራት መቀነስ ሊያጋጥም ይችላል ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አገልግሎት ሳይቆራረጥባቸው በተቻለ ፍጥነት እና ጥንቃቄ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን በማዘዋወር፤ እንዲሁም አዳዲስ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ግንባታ በማከናወን አገልግሎት ለማስቀጠል ጥረት እያደረግኩ ነው ብሏል።

ይሁን እንጂ ኩባንያው የአገልግሎት ጥራት የሚኖርባቸው የተለዩ አካባቢዎችን አልጠቀሰም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ እንደገለጹት በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ግንባታ በስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል።

መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply