ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት ዓመት 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች 66.5 ሚሊየን መድረሱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

በበጀት አመቱ 64 ሚሊየን ተጠቃሚዎችን ለመድረስ ታስቦ 18.4 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 66.5 ሚሊየን ተጠቃሚዎችን መድረስ መቻሉን እና ይህም የእቅዱን 105 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

ከህዝብ አሰፋፈር አንፃር 99.1 በመቶ መድረሳቸውን እንዲሁም 63.3 በመቶ የቴሌኮም አገልግሎት የደረሰባቸው መሆናቸውንም አንስተዋል።

የተለያዩ አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥርም እየጨመረ መሄዱን ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፤ የሞባይል ድምፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር 64.5 ሚሊየን ፣ የሞባይል ኢንተርኔት 25.6 ሚሊዮን እና የዋይፋይ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ 506 ሺህ መድረሱን ገልጸዋል።

የአገልግሎት መቋረጥ ፣ የደህንነት ችግር ፣የሃይል አቅርቦት ፣የነዳጅ እና የዋጋ ግሽበት በበጀት አመቱ የታለመውን ያህል ማሳካት እንዳይቻል ያደረጉ ምክንያች በሚል ተጠቅሰዋል።

በእነዚህ ሁሉ ችግሮች መሃል እንኳን ሆኖ 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን እና 18.8 ቢሊየን ብር ግብር መክፈላቸውንም አንስተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከአለም የኦፕሬተሮች ቁጥር 26ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ ከናይጄሪያ በመቀጠል 2ኛ መሆኑንም ሰምተናል።

በእስከዳር ግርማ

ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply