ኢትዮ ቴሌኮም ከአድቫንስድ 4G 20 እጥፍ ፍጥነት ያለውን የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት ተግባራዊ አደረገ።የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ እንዳሉት የ5G አገልግሎት በፋይናን…

ኢትዮ ቴሌኮም ከአድቫንስድ 4G 20 እጥፍ ፍጥነት ያለውን የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት ተግባራዊ አደረገ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ እንዳሉት የ5G አገልግሎት በፋይናንስ ተቋማትም ሆነ የጤና ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በሀገራችን የጤና አገልግሎትን በርቀት ሆኖ በመስጠት ተደራሽ ለማድረግ ያግዛልም ብለዋል።

ለማዕድን ፍለጋና በሮቦት ለታገዙ ስራዎች ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አንስተዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ 70 ሀገራት በአፍሪካ ደግሞ 5 ሀገራት ይህን አገልግሎት ተግባራዊ ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያም ይህን አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች።

ዩኒቲ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ ሸራተን አዲስና የቸርችል ጎዳና እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም መስሪያ ቤት አካባቢዎች የ5 G አገልግሎት ተግባራዊ የሆነባቸው አካባቢዎች መሆናቸው ታውቋል።

በሙሉቀን አሰፋ

ግንቦት 01 ቀን 2014ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply