ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን/ ማርች 8ን/ ምክንያት በማድረግ በጽዳት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሴት ሠራተኞች ዘመናዊ ስልኮችን አበረከተ፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን/ ማር…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/OYxKg1_FWhAHD_MDTb2KPLHaQEXvhyIx9pC_g6GkIiNalXz5kQg6H0oW_BVgkrYzrQfHMU5EeTSArQlMZt87iVifHT4zS3N_K4u6HUOY2heaIxNdKfxVCnbt3cHKIyQBet-Iid3YmM7vDkHw51-JXgJsmeNQ5NhE9Bimm9TnbE5kjX3GhM_wv08qg0Pi_N7PgidA_McLAj8ZCNtfaHWhiXXxOIKtL2wkpMYnwvp388qCqjK2Du9MtIhu_MZYvXe4ktPJcpPohosKbgMiDuLq9WwRN1lPCD68klpgbHsCJx4sYocb1dd11-rhJcmf-whqY6H3CWAQ-U3B_B1R0C0Alw.jpg

ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን/ ማርች 8ን/ ምክንያት በማድረግ በጽዳት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሴት ሠራተኞች ዘመናዊ ስልኮችን አበረከተ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን/ ማርች 8ን/ የዲጂታል አካታችነት ለፆታ እኩልነት በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት አክብሯል፡፡

በዚህም ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ ስልኮችን ከ122 ወረዳዎች ለተውጣጡት 353 ሴት የጽዳት ሠራተኞች በዛሬው እለት ሸልሟል፡፡

ሽልማቱ ሴቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚ አካታችነትንና እኩልነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ሲሉ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡

ሴቶችን ማካተትና ማብቃት የኩባንያችን አንዱ እሴት እና መገለጫ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣የዛሬውን ሳይጨምር ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ ሴቶች የመረጃ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል 54.4 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ከ70 ሺህ በላይ የሞባይል ቀፎዎችን መስጠትን ጨምሮ በትምህርት ቤቶችም የተለያዩ ማህበራዊ ሃላፊነቶችን ኩባንያው እየተወጣ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው እለት የሚታሰበውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገበት እና ለ2 ቀናት የሚቆይ የሴቶች ጥቅል ያዘጋጀ ሲሆን፣ ጥቅሉን ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር በቴሌብር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል እና በ999# ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply