ኢትዮ ቴሌኮም ያሻሻለው የ”ቴሌብር ሱፐርአፕ” መተግበሪያ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?-ይህ አዲስ መተግበሪያ አሁን በሥራ ላይ ካለው የቴሌብር መተግበሪያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የአፈጻጸም፣ የሴኩ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/jY9plPJPQloWQkYtSlevJYjuXSzqw4mnD5UZg3xH2eDM0Wuf4KOvqydljCqCaFgBKAo8YzP-NX69DdgEWGvsN-Yps_pC-oYUZgLBh3C3RdbCo_hOO2YKKstsv10lK8A88CIw-a2HpvXosdnIukHYJa_7G2aNkJi9yXhABvAmjIsMJgA_5g25enkV78hpRkrsN2juRH2FUDDvFTg1w5dTAmKqn4dbLyZSiFKjb03xVXZMn28RyFmCg60RBc43YqQnP5gO-mUUWpSzvjkmh4t6jPwxIPnfc0p6rClsRFCYBZb6bVZoq5nMr46d8eGQRmSuohsNDpCdRyWQk2WqkkBkAA.jpg

ኢትዮ ቴሌኮም ያሻሻለው የ”ቴሌብር ሱፐርአፕ” መተግበሪያ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?

-ይህ አዲስ መተግበሪያ አሁን በሥራ ላይ ካለው የቴሌብር መተግበሪያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የአፈጻጸም፣ የሴኩሪቲ ሲስተም፤ ወደ ሲስተም ማስገቢያና ምዝገባ ጊዜ የተለያዩ መተግበሪያዎችን በማውረድ የስልክ የዳታ የመያዝ አቅም መቀነስ እና የመሳሰሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፤

-ቴሌብር ሱፐርአፕ (Telebirr Super App) በዕለት ተዕለት ኑሯቸው የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችንና አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ ታግዘው ለደንበኞች ለማድረስ የሚስሩ ቢዝነሶችን ለማገዝ ታስቦ የበለጸገ መተግበሪያ ነው፤

-የቴሌብር የፋይናንሻል አልግሎት፣ ኢኮሜርስ እና አነስተኛ መተግበሪያዎችን እንዲሁም ሶሻል ኔትዎርኪንግ እና የህይወት ዘይቤ የመሣሠሉ አገልግሎቶችን በማቅረብ ደንበኞች በአንድ ጊዜ ፈርጀብዙ የዲጂታል ግብይት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል፤

ኢትዮ ኤፍ ኤም ባገኘው መረጃ መሰረት ቴሌብር ባለፉት 22 ወራት ብቻ ከ101 ሺ በላይ ወኪሎች፤ ከ28 ሺህ ነጋዴዎች እንዲሁም ከ19 ባንኮች ጋር ትስስርን የፈጠረ ሲሆን፣ከ44 አገራት ከ1.95 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማድረጉ ታውቋል፡፡

በእስከዳር ግርማ
መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply