ኢትዮ አውቶሞቲቭ የመኪና አያያዝ እና አጠቃቀም ክፍል 1 መፅሐፍ ሊመረቅ ነው።በአውቶሞቲቭ ዙሪያ የተዘጋጀው “ኢትዮ አውቶሞቲቭ የመኪና አያያዝ እና አጠቃቀም ክፍል 1” መፅሐፍ የፊታችን ቅዳሜ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/s2K6mgSnrjZuSf3P5Hl6sLy1IP5M4576_-_mniDkkJeGhBE-y9ZLNb6X2GWcy45n_EEtUKQT2hbiSjmWl990G_LAm-BhG-vVLx1i2cdR4kKRmYMTu4REJFmiW8-VLv7my1_RPPrX7Oxe8VBYaMk8Rsz5PaHqCi49wznrj2AxPUyAcQPBovJ7NfXQZjZF1MjHlFvxpWxhZ-jDIDIZYxN5JXbmjWdsGtGoV406TuT8MehsfuNC6UbYJqSgL8LTi08hx__QsBTX6WRhn2Luw-QWIOBITfvLzq3jmVK-dYyPbZ8iFaSaWNFxKqTbCLh0ubwU88-VLJBk8CFAy1WnlR2vLA.jpg

ኢትዮ አውቶሞቲቭ የመኪና አያያዝ እና አጠቃቀም ክፍል 1 መፅሐፍ ሊመረቅ ነው።

በአውቶሞቲቭ ዙሪያ የተዘጋጀው “ኢትዮ አውቶሞቲቭ የመኪና አያያዝ እና አጠቃቀም ክፍል 1” መፅሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም ይመረቃል ተብሏል።

ለመኪና ባለቤቶች፣ ለጥገና ባለሙያዎች ፣ ለመለዋወጫ እቃ አቅራቢዎች ፣ በመኪና ንግድ ለተሰማሩ ፣ ለተሽከርካሪ ስምሪት እና ትራንስፖርት ባለሙያዎች እንዲሁም በትምህርት ፣ ጥናት እና ምርምር ላይ ለሚሰሩ ሁሉ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የተገለፀው።

የመፅሐፉ ደራሲ ዶ/ር ኢንጂነር ዳንኤል ጥላሁን ለዚህ መፅሐፍ መነሻ የሆነው በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ ላይ የሚቀርበው ኢትዮ አውቶሞቲቭ የሬዲዮ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል።

መፅሀፉ የመኪኖችን ደህንነት እንዴት መጠበቅ ይገባናል የሚለውን እንዲሁም አዳዲስ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል የሚለውን እና የቴክኒክ ጉድለቶች ሲያጋጥሙ ምን ይደረግ የሚለውን የሚዳስስ መሆኑን ገልጸዋል።

በነዳጅ ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ባሻገር በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ጭምር የሚሆኑ ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘ መሆኑን የመፅሀፉ ደራሲ ተናግረዋል።

መፅሀፉ 7 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን አንደኛው ምዕራፍ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ነው ያነሱት።

መፅሀፉ 7 ምዕራፎች፣ 165 ገፆች ፣ ከ60 በላይ ስዕላዊ መግለጫዎች ፣ ከ30 በላይ በሰንጠረዥ የተዘጋጁ መረጃዎችን እና ከ35 በላይ ማጣቀሻ መፅሀፍትን ያካተተ ሲሆን በአማርኛ ቋንቋ ተፅፏል።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply