ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቅርቡ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እና ማሽኖችን ወደ መገጣጠም እንደሚዘዋወር ተገልጿል፡፡በነ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/LjLBQ3Vt6K78lPBCyjSCVy-L-5RZU8KxZLY9CKT6S5uiffQ228j9hDK35WJQF14hX5pif05hOyRfwydGzKWgUe9J_bMsQ5sTrtMxElX_e0igAiu6R3sbYOFN0tA0LWFMbJEol4sm2f1AO6nuIaIit6NZNQ2YKj61t2YrAn_Wz1-j1OhbSXy9uau0o3mIUZ75zLlrPyXGFTz86f49wTiSSQbPXow251Nh0AzS7g3HsdFkPIeJUSBMqi39ydr7D5C8LXsci6xUnUk1zxhS4JBrJgxLvfJZELCRsmzmZOJl3pasIv90o4Er3-b4Y-V8yteroFq6kDUYYl41VZWrP8Cyuw.jpg

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቅርቡ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እና ማሽኖችን ወደ መገጣጠም እንደሚዘዋወር ተገልጿል፡፡

በነዳጅ እና ቤንዚን የሚሰሩ መኪኖችን መገጣጠም ከዚህ በኋላ አስተማማኝ ስራ አይደለም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ ወደሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ፊታችንን ማዞር አለብን ብለዋል፡፡

ከዉጪ የሚገቡ በነዳጅ እና ቤንዚን የሚሰሩ መኪኖችን ለማቆም ዉሳኔ ላይ የተደረሰዉ በአገር ዉስጥ ያሉ ትላልቅ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማበረታታት ነዉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕም እንደዚሀ ዓይነት መኪኖችን ለመገጣጠም አቅም እና ልምድ ያለዉ ነዉ ብለዋል፡፡

የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር ሱለይማን ደደፎ በበኩላቸዉ ፤ ግሩፑ የተለያዩ መኪኖችን እና የኢንዱስትሪ ማሽኖችን መግጠም በሚችልበት ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሚያዝያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply