ኢትዮ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊዘጋጅ ነው

የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ኘሮሞሽንና ኢቨንት  እና ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ከሰኔ 5 -9 የሚቆይ ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም በቅርበት እንዲያውቁት የሚያደርግ ፌስቲቫል እንደሆነ ተገግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ፌስቲቫሉ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ቱሪዝምን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ሰምተናል፡፡

በፌስቲቫሉ ላይ የተለያዩ የሀገራችን ክልሎች ምግቦች እና መጠጦች ለታዳሚው እንደሚቀርቡ እና ልዩ ልዩ የውይይት መድረኮች፣ የእርስ በርስ ግንኙነት መፍጠሪያ ፕሮግራሞች እና አዝናኝ ዝግጅቶች የፌስቲቫሉ ዋና ዋና መርኃግብሮች ናቸው ተብሏል ።

የፊስቲቫሉ መግቢያ በነፃ መሆኑን እና ሁሉም ህብረተሰብ መካፈል እንደሚችሉ ተነግሯል ።

የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል በኢንዱስትሪ ልማቱ ላይ ድርሻ ካላቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት በምርምርና ስርአት ፣በቴክኒክ ምክር እና ድጋፍ ፣በመረጃ ፣በገበያ በስልጠና ኢንዱሰትሪዎችን በማገዝ የበኩልን አስተዋዕኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ማዕከል ነው።

የኢትዮ ምግብ መጠጥ ፌስቲቫል ተባባሪ አካላት የሆኑት አሚዚንግ ኘሮሞሽንና ኢቨንት እንዲሁም ዳብ ትሬዲንግ በሁነት ዝግጅት ፣በቴሌቪዥን ፣በሬዲዮና ህትመት ማስታወቂያ ኘሮሞሽኖች ሰፊ ልምድ ያላቸው ሲሆን ለአመታት ያዳበሩትን ልምድ በመጠቀም ፌስቲቫሉን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ  ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል ።

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply