
ኢትዮ 251 ሚዲያ ተዘረፈ! የአማራ ሚዲያ ማዕከል መጋቢት 11 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮ 251 ሚዲያ ካሜራን ጨምሮ ሙሉ የሚዲያ ንብረቶቹን ተዘረፈ። ዘረፋው ትናንት ዕሁድ መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ/ም ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት የተፈጸመ ሲሆን የድርጅቱ መገልገያ የነበሩ አራት ዘመናዊ ካሜራዎች፣ ኔክማይክ፣ ዙመር እና ሌሎችም መገልገያ ቁሳቁሶች ተዘርፈዋል። ቁሳቁሶቹ አራት ኪሎ ሚዲያን ጨምሮ ነገረ ወልቃይት ጭምር የሚገለገሉባቸው ነበሩ። የሚዲያ ፕሮዳክሽን ቁሳቁሶቹ ትናንት እሁድ ዕኩለ ቀን ድረስ ሲሰራባቸው ነበር ያለው የኢትዮ 251 ሚዲያ ባለቤትና ስራአስኪያጅ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር የተዘረፉት ንብረቶች አጠቃላይ ዋጋ ከአንድ ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ተናግሯል። ኢትዮ 251፣ አራት ኪሎ ሚዲያ እና ነገረ ወልቃይት ሚዲያ ወቅታዊ ሃገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን በመዘገብና ጥልቅ ትንታኔዎችን በመስጠት ከሚታወቁ ቀዳሚ የዲጂታል ሚዲያ አማራጮች መካከል መሆናቸው ይታወቃል።ምንጭ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር
Source: Link to the Post