ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY ከኦሮሙማ ማኔፌስቶ! የመንግሥት መዋቅር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጣልቃ ገብነት መላቀቅ አለበት!(ክፍል ሁለት) ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

የፊንፊኔ  ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የፊንፊኔ  ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የኦሮሙማ ማኔፌስቶ!!!

መንግሥት መዋቅር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ መሆን አለበት!!! ለአዲስ አበባ ራስ-ገዝ አስተዳደር

‹‹ መንግሥት የሆነ አካል …የሆነ አካል ድምፅ ስላሸነፈ ወይም ስላሸነፉ ….ጥምረት የፈጠረ መንግሥት››

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው አሯሯጭ (Pacemakers) ወይም አጫፋሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫ ራሳችሁን አግልሉ እንላለን፡፡ የምርጫ ሂደቱ ነጻና ገለልተኛ ያልሆነ የዶሞክረሲ መርህ ያልጠበቀ፣ የኦሮሚያ ክልል በር ዘግተው በብቸኛነት ኦዴፓ ብልፅና ፓርቲ ምርጫውን ያለተወዳዳሪ እንዳሸነፈ ታውቆል፡፡ የዓለም አቀፍ ህረተሰብና መንግሥታት ለሃገራችን ምርጫ እውቀና እንደማይሠጡትና ታዛቢ ለመሆንም ፍቃደኛ አለመሆናቸው አስታውቀዋል፡፡ ሦስት ክልሎች በምርጫ  በማይሳተፉት (ትግራይ ፣ሱማሌና ሃራሪ)፣ ቤኒሻንጉል በግማሽ፣ በደቡብ ወላይታ ምርጫ የለም፣ በአማራና በወለጋ  የተወሰኑ ቦታዎች ምርጫ የለም፣ በኦሮሚያ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከምርጫ ራሳቸውን አግለዋል ብልፅግና ፓርቲ ብቻውን በሚወዳደርበት በተጨማሪም በሃገሪቱ ስባት  ቦታዎች በኮማንድ ፖስት ወታደራዊ አገዛዝ  ሥር ህዝብ ተጠርንፎ እየተሰቃየ ሳለ፣ ከስምንት መቶ ሽህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች በምርጫ መሳተፍ ባልቻሉበት፣ ሃገሪቱ በርሃብ ቸነፈር  እንዳትመታ ስብዓዊ እርዳታ  በሚያስፈልግበት ሰዓት፣ በኤርትራ ሱዳን ሉዓላዊነታን በተጣሰበት ጊዜ ሠላም ሳይኖር ምርጫ የሚፈይደው አንዳችም ነገር የለ እንላለን፡፡

 

ሰኔ 15 ቀን 2013ዓ/ም ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፎል!!!

አምስቱ ፓርቲዎች በጋራ የሠጡት በአንዱ አፍ መግለጫ በዚህ ምክንያት ምርጫው ቁቡልነት የለውም አንድ ሦስተኛ የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫው አይሳተፍም፡፡ ሰኔ 15 ቀን 2013ዓ/ም ኦዴፓ ብልጽግና ኢዜማ መንግሥት ለመመሥረት ለሚያስችላቸው ድምፅ አግኝቶል፣ በምርጫው ለተሳተፉ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ሁሉ እናመሠግናለን፡፡ ይሎችሆል፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫው ጥላችሁ በመውጣት (boycott) ታሪክ ካልሰራችሁ፣ በ2014ዓ/ም ከምርጫው በኃላ የፊንፊኔ  ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የፊንፊኔ  ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳችሁ እንገናኛለን፡፡ ከ2013 ዓ/ም 2014 ዓ/ም የከፋ እንዳይሆን ለአዴፓ ብልፅግና ፓርቲና ኢዜማ  አገዛዝ በምርጫ አሸናፊነት እውቅና መስጠታችሁን አንዘንጋ፡፡ በሦስት አመታት የሃገራችን ዜጎችን በግፍ እየታረዱ ማስቆም ያልቻለ መንግሥትን ተጨማሪ አምስት አመታት መስጠት በዜጎች ነፍስ መቀለድ ነው!!! እንደ ወያኔ ኢህአዴግ፣ ኦዴፓ ብልፅግናም መወገድ አለበት!!!የዓለም መንግሥታትም ፊት ነሰቶታል፡፡ ጊዜው አሁን ነው!!! የቅድመ ምርጫ መግለጫ በዝቅተኛውን ደረጃ እንኮን አለማሞላቱን ለህዝብ ገልፀው እንደዛም ሆኖ የብልጽግና ፓርቲ አሯሯጭ (Pacemakers) ሆነው መጨረስ እንደሚፈለጉ ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡ በምርጫው ሂደቱ እክል እንደነበረው ገልፀው ‹‹ መንግሥት የሆነ አካል …የሆነ አካል ድምፅ ስላሸነፈ ወይም ስላሸነፉ ….ጥምረት የፈጠረ መንግሥት›› እያሉ በተንደፋደፈ ምላስ አፍ ውስጥ ውሸት ተስተውሎል፡፡ አምስቱ ፓርቲዎች በጋራ የሠጡት በአንዱ አፍ መግለጫ  የብልጽግና ፓርቲ እንደአሸነፈ እያወቁ እንዳላወቁ የማስመሰል ፖለቲካቸውን ህዝብ እንዳልወደደላቸው ይወቁት፡፡ የአብይ መንግሥት ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ገና ከሂደቱ ጦሴ ጥንቡሳሴ ብሎ በአፍጢሙ ጥሎታል ባሉበት አፋቸው  ‹‹መንግሥት የሆነ አካል›› እያሉ የኦዴፓን ብልፅግና ሥም ላለመጥራት ያደረጉት ንግግር እራሳቸውን ከማታለል ያለፈ ማንንም አያታልሉም ‹‹ዶሮን ሲያታልሎት በመጫኛ ጣሎት›› ከእንግዲህ ስለ ምርጫ ያነሳ ‹‹የውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን!!!›› ብለናል፡፡ (አምስቱ ፓርቲዎች በጋራ የሠጡት መግለጫ (ኢትየዮ ኒውስ) በ2014ዓ/ም አምስቱ ፓርቲዎች በጋራ የሠጡት አዲስ መግለጫ እንደ ልብወለድ የተደረሰ፡፡

 

የኦዴፓ ብልፅግና የዘረኝነትና የተረኛነት የኦሮሙማ ማኔፌስቶ!!!

‹‹  OBN  ግንቦት 17 ቀን 2013  የፊንፊኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በይፋ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ፕሬዝዳንት አቶ ኩመላ ቡላ የፊንፊኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፍርድ ቤቶች አደረጃጀት ሥልጣን እና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 216/2011ን መሠረት በማድረግ በይፈ ተከፍቶ አገልግሎ መስጠት መጀመሩን ለ OBN  ተናግረዋል፡፡ የፊንፊኔ ከተማ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልሉን መንግሥት መቀመጫ ከመሆኖ ጋር ተያይዞ የክልሉን መንግሥት የተመለከቱ ወንጀል ነክና የፍትሃ ብሔር  ጉዳዩችን በዚህ ፍርድ ቤት ይታያሉ ብለዋል፡፡ የፊንፊኔ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችንም ሕገ መንግሥታዊ መብቸውን በመቀም ዚህ ፍርድ ቤት በቌንቌቸው የመዳኘትና ተደራሽ የሆነ የፈትህ አገልግሎት ኘት መብትም ያገኛሉ ብለዋል፡፡ የፊንፊኔ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ከአሁን በፊት ፍትህ ለማግኘትና በቌንቌቸው ለም ገንዘባቸውንና ጊዜቸውን በማባከን በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወደሚገኙ ፍርድ ቤቶች ሲመላለሱ እንደነበር የተናገሩት ፕሬዜዳንቱ  ይህ ፍርድ ቤት በይፋ ተከፍቶ ሥራ መጀመሩ ግን ይህንን እንግልትና ውጣ ውረድ ያስቀራል ብለዋል፡፡ በፍርድ ቤት የአገልግሎት ማስጀመርያ መርሃ ግብር ላይም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ የኦሮሚያ ማረምያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል››

‹‹ይህ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ተቋማት የሚኖራቸውን የወንጀል እና የፍታብሄር ጉዳይ የማየት ስልጣን አለው ተብሏል።

√√ ተቋማቱ ከማን ጋር ፣ በምን ጉዳይ የሚኖራቸውን ጉዳይ ነው የሚመለከተው??? ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ጋርስ እንዴት ታይቷል?

 • •• በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በቋንቋቸው የመዳኘት መብት በዚሁ ፍርድ ቤት ይተገበራል ተብሏል።

√√ በምን ጉዳይ? ወንጀል?  ፍታብሄር?  ከማን ጋር በሚኖራቸው ክርክር?  ከፌደራል ህጎችስ ጋር እንዴት ታይቷል?

 • •• ፍርድ ቤት ከመንግስት የስልጣን ክፍፍሎች አንዱ ነው። ይህ ፍርድ ቤት የተቋቋመው በኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 216/ 2011 ይመስለኛል። እናም የዚህ ፍርድ ቤት ስልጣን ከህገ መንግስቱ ፣  ከአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር እና ከፌደራል አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር  በምን መልኩ ታይቷል!!!››……………(1)

The city government has the city courts and woreda social courts. The city courts have a first instance court and an appellate court. The jurisdiction of the courts is stipulated in the city charter. The Federal Supreme Court decides on conflict of jurisdiction that may arise between the Addis Ababa city courts and federal courts.

 

#1- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፡- የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ተከሳሾች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፍርድ ቤት በግድ በማዘዋወር መክሰስ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌውን ከአዲስ አበባ በግድ ወስዶ ወደ ብሸፍቱ ፍርድ ቤት በማዘዋወር ለስድስት ወራት ማሰርና ማሰቃየት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት መአዛ አሸናፊ  የክልሎቹንም ፍርድ ቤቶች በዘር ላይ የተመሠረተ አፓርታዳዊ የፍትህ ሥርዓት  በመገንባት በኢትዮጵያ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ አኑራለች፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከላይ እስከታች በአንድ ዘር ስልጣኑን ተቀራምተውታል፡፡ ተመሥገን ደሣለኝ ፍትህ መጽሄት የተቋሙን ወረራ ባጭሩ ዳስሷል።

 • የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት መአዛ አሸናፊ – ኦሮሞ (2) የፌጠ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ፦ሰለሞን አረዳ – ኦሮሞ (3) የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ጽ/ቤት ሃላፊ፦ቦጃ ታደሰ – ኦሮሞ (4) የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ጌታሁን አለማየሁ(ዶር.) – ኦሮሞ (5) የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮርት ማኔጀር ጽ/ቤት ሀላፊ ነሙ አዱኛ – ኦሮሞ (6) የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ፦ዘሪሁን ጌታሁን – ኦሮሞ (7) የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሀላፊ ፦ብርሀነመስቀል ዋጋሪ – ኦሮሞ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ፦ ተስፋየ ነዋይ – ኦሮሞ

 • በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80/3 ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው ሰበር ችሎት (3ሰበር ችሎቶች አሉን) በ5ዳኞች ብይን የሚሰጥ ሲሆን እነዚህን ዳኞች የሚመርጡት የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንቷና ምክትሏ ናቸው።(ከላይ 1ና2ን እይ)

የኦሮሙማ ማኔፌስቶ!አዲስ አበባ ከተማን ለመሰልቀጥ  የአፓርታይድ ህግና ተቆም በመመስረትየፍንፍኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት!› በአዲስአበባ ከተማ ውስጥ አቆቁመዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫ ዉጡ!ህገ-መንሥቱ ተጥሶል፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ እራሱን በእራሱ የማስተዳደር ነፃነቱን በኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ  የዘረኛና ተረኛ ስሜት ‹‹ፊንፍኔ ኬኛ!!!››   በማለት ይፎክራሉ፡፡ አዲስ አበባ ኢትዮጵያውያን በጋራ ለዘመናት በጋራ የገነቦት ከተማ ናት፡፡  የአማራ ህዝብ፣ የትግራይ ህዝብ፣ የኦሮሙ ህዝብ የሱማሌ ህዝብ፣ የአፋር ህዝብ፣ የጋምቤላ ህዝብ፣ የቢኒሻንጉል ህዝብ፣ የሃረሪ ህዝብ፣ የሲዳማ ህዝብ፣ የደቡብ ህዝብ፣ ከባርነት ሠንሠለታችሁ በቀር የምታጡት አንዳች ነገር የለም፡፡ ከርሃብ፣ በሽታ፣ ስደትና፣ ጦርነት በቀር የምታጡት የለም፡፡ በህዝባዊ አመፅና እንቢተኛነት ወያኔ ኢህአዴግን እንዳስወገድን ሁላ ኦዴፓ ብልጽግና  ፓርቲን ዘረኛና ተረኛን ለመጣል ቆርጠህ ተነሳ፡፡

ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ እስከመቅኒያቸው ድረስ በሙስና የተዘፈቁ፣ ዓይን አውጣ ሌቦች ሃገራችን በዚህ ሦስት አመት ውስጥ እንዲህ በስልጣን የባለጉ ሹሞች አይታ አታውቅም፡፡ የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ አስተዳደርን በበቃን ህዝባዊ አመፅ ማስወገድና የውይይትና ድርድር  የጋራ መድረክ ማዘጋጀት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ በመጀመሪያ ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቶቹ መከበር በአስተማማኝ ሁኔታ መከበርና ገዳዬቸ አራጆች ታድነው ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በዘርና ቌንቌ ላይ የተመሠረተ ፌዴራዝም በተወላገደ መንገድ የተረጎሙትን የህወሓት ኢህአዴግና የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ አድሎዊ የዘር አገዛዝ ተላቀን ሁሉም ብሄሮችና ብሔረሰቦች በእኩልነትና በነፃነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ህገመንግሥት ማርቀቅ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡

 

#2- የአዲስ አበባ ፖሊስ፡- የአዲስ አበባ ከተማ  አጠቃላይ ወጪ ለመንገድ፣ለትምህርት፣ ለውኃ፣ ለጤና፣ ለከንቲባ፣ ለመሬት፣ ለፖሊስ፣ ለቤት ግንባታ፣ ለገቢዎች ባለሥልጣን፣ ለንፅህና አገልግሎት ቢሮ፣ ለአንበሣ አውቶብስ፣ ሸገር ባስ፣ እና ለለሎች አገልግሎቶች ወጪ ያወጣል፡፡  የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከንዋሪዎቹ የተመለመሉ ፖሊስ ኃይል የነበረው ሲሆን ከ 1997 ዓ/ም ምርጫ በኃላ በህወሓት /ኢህአዴግ መሪ በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ ህገ-ንግሥቱ የፈቀደለትን መብቶች ተጥሰዋል፡፡ የፖሊስ ኃይሉ ከክልሎች እንዲመለመሉ በማድረግ የአዲስ አበባ ህዝብ መብቶ ተጥሰው ይገኛሉ፡፡  የአዲስ አበባ ህዝብ የእራሱ ፖሊስ ሠራዊት የለውም፡፡ ለአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ ክልሎች የተመለመሉ የፖሊስ ሠራዊት በመዋጮ ይሠፍሩበታል፡፡ ከ1997 ዓ/ም ምርጫ በኃላ የፖሊስ ሠራዊቱ ከህዝብ ጋር አብሮል በማለት ህዝባዊ ፖሊስ ኃይል በወያኔ ኢህአዴግ ዘረኛ ጠርናፊዎች ዛሬም በኦዴፓ ብልጽግና ዘረኛ ተረኛ ፖሊሶች በግፍ ይተዳደራል::‹‹መከረኛዋን አዲስ አበባ በ10ሩም ክ/ከተሞች 10 ፖሊስ መምሪያዎች አሏት። ከ10ሩ 2ቱ ከደቡብ፣ 2ቱ ከአማራ፣ 1ከተጋሩ ሆኖ ቀሪዎቹ 5ቱን በኦሮሞ አዛዦች የተያዙ ናቸው። በከተማዋ ካሉ 60 ፖሊስ ጣቢያዎች 26ቱ የኦሮሞ አዛዦች ተቆጣጥረዋቸዋል።– የከተማዋ የሚዘዋወሩ ፖሊሶች ስብጥራቸው እንዴት ነው ካልክ ( FB ህን ዝጋና በሸገር ጎዳናዎች ትንሽ ወክ አድርግ።››ፍትህ መፅሔት

 

#3-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዳክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ተጠያቂ የሌለበት  ሥር የሰደደ ሙስና፣ 

“The mayor is the chief executive officer of the city and is accountable to the city council and the federal government. The mayor is elected by the city council from among the members, for the same term as the council. The city cabinet is accountable to the mayor and is responsible to ensure that proclamations, regulations, resolutions, and standards adopted by the city council and by the federal government are implemented.”

 • የአዲስ አበባ ጥናት መቶ ሃያ ሁለት ሽህ ሄክታር መሬት ከአዲስ አበባ ክልል ተወስዶ ወደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ማዘዋወር ታቅዶል፡፡ ከስድስት ክፍለ ከተሞች ሠላሣ ወረዳዎች ወደ ኦሮሚያ ለማዘዋወር ተቅዶል፡፡ በዚህም መሠረት ከየካ ክፍለከተማ ስድስት ወረዳ፣ ቦሌ ሁለት ወረዳ፣ ጉለሌ አምስት ወረዳ፣ ንፋስ ስልክ አንድ ወረዳ፣ አቃቂ ሰባት ወረዳዎች፣ ኮልፌ ቀራኒዬ ዘጠኝ ወረዳዎች ናቸው፡፡ ኢዜማ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ቢሮቸው ሄዶ መጠየቅ ይጠበቅበታል፡፡
 • ኢንጅነር ተሃከለ ኡማ 460 ሽህ ካሬ ሜትር የታጠረ ቦታ ለ150 አርሶ አደሮች ተመልሶል፡፡ በአርሶአደሮች ስም ዲያስፖራዎችና የኦዴፓ ካድሬዎች በዚህ ቅርምት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር መሬት ሰጪም በጉልበት ነጣቂም መሆኑ ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ ንብረት መንጠቅ የህግ ጥሰትና አድሎዊና ዘረኛ አመለካከት ብዙ ዜጎችን በድሎል፡፡
 • ኢንጅነር ተሃከለ ኡማ አስተዳደር 14000 (አስራ አራት ሽህ) ኮንዶምኒየም ቤቶች ለአንድ ብሄረሰብ አባላት ለኦሮሞ የመንግሥት ሠራተኞች አስር ሽህ ብር ለእጣ በማስከፈል በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ፕሮጀክት አራት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አቶ ስንታየሁ ቸኮል አጋልጠዋል፡፡ ኢዜማ!!!

‹‹የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ከታከለ ኡማ ወደ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና ባለቤት አልባ ህንፃዎች እንዲሁም ኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ዙሪያ የተደረገ የማጣራት ውጤት ላይ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም 1,338 ሄክታር መሬት በሕገ-ወጥ የተወረረ መሆኑን፣ 21,695 የጋራ መኖርያ ቤቶች በተለያየ በሕገ-ወጥ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን፣ 322 ግንባታቸው ያለቀና ያላለቀ ህንፃዎች ባለቤት አልባ ሆነው መገኘታቸውን፣ 14,641 መኖርያና ለንግድ የተከራዩ የቀበሌ ቤቶችን ያለ አግባብና በሕገ-ወጥ ይዞታነት የሚገኙ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማክሰኞ እለት፣ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ 13 ሚሊየን 389 ሺህ 955 ካሬ ወይም 1 ሺህ 338 ሄክታር መሬት በሕገ-ወጥ መያዙን አስታውቀዋል።

ወይዘሮ አዳነች በዚህ መግለጫቸው ላይ እንዳሉት በአዲስ አበባ በሕገ-ወጥ መንገድ ከተያዙት 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 15 ሺህ 891 የሚሆኑት የባለቤትነት መረጃ አልቀረበባቸውም።

850 ቤቶች ደግሞ ዝግ ሆነው ሲገኙ 4 ሺህ 530ዎቹ ደግሞ ባዶ ሆነው ተገኝተዋል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።

እንደ ምክል ከንቲባዋ መግለጫ ከሆነ 424 በሕገ-ወጥ መልኩ በግለሰቦች ተይዘው የሚገኙ ሲሆን በዕጣ ሳይሆን በተለያዩ አግባቦች ወደ ተጠቃሚው ግለሰቦች የተላለፉ ደግሞ 51 ሺህ 64 ቤቶች ሆነው ተገኝተዋል።››………(2)

 

ዶክተሮች ሥራ አጥ የሆኑበት ሥርዓት መነቀለ አለበት! የፖለቲካ ካድሬዎች ዘመን ማክተም አለበት!!!

#4- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሥራ አጠ ወጣቶች ቁጥር በ20/ 2015 እኤአ 22.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ 2016/2017 እኤአ 14.55 በመቶ ዝቅ ብሎ ነበር፡፡ በከተማው የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም በ2016/2017 እኤአ 29.6 በመቶ የነበረ ሲሆን ወደ 18.9 በመቶ ዝቅ ብሎል፡፡  Unemployment has been reduced from 22.9 percent in 2014/2015 to 14.55 percent in FY2016/2017. Poverty has reduced to 18.9 percent from 29.6 percent in FY2016/2017. የአዲስ አበባ የከተማው ልማት መርሃ ግብር ዓላማና ግብ ለትውልዱ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለግሉ ዘርፍ ኢንቨስትንት እንዲስፋፋ ሁለንተናዊ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና የጠቃቅንና አነስተኛ ኢነተርፕራይዞችን እድገት ማመቻቸት፣ የመኖሪያ ቤቶችን መገንባት፣ የቁሻሻ አወጋገድ አስተዳደርን ክህሎት ማሳደግ፣ የተለያዩ በሽታዎችን ኤድስ፣ ኮሮና ወዘተ በሽዎችን መከላከል ያካትታል፡፡ በአዲስ አበባ ክልላዊ መንግሥት 1,255,486 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ሽህ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት) የሥራ  አጥ  ይገኛሉ፣ 419 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር:: በህወሓት ኢህሰዴግና በኦህዴድ ብልፅግና የግፍ አገዛዝ ዘመን የአዲስ አበባ ከተማ ንዋሪዎች በፖሊስ ሠራዊት ተመልምለው የሥራ ዕድል እንዳያገኙ ተደርገዋል፡፡ በከተማዋ ባሉ አስር ክፍለ ከተሞች ውስጥ ያሉ የሥራ ዕድሎች ትላንት በወያኔ ዛሬ በኦህዴድ ብልጽግና ያለአንዳች ውድድርና እውቀት በዘር መታወቂያ ይታደላል፡፡ የአዲስ አበባ ንዋሪዎች በስራ አጥነት ህይወትና በቤት ኪራይ ውድነት፣ በልማት ተነሽነት ወዘተ ችግሮች ላለፉት ሠላሳ አመታት ሲሰቃይ ኖረዋል፡፡

በመላ ሃገሪቱ ያሉ ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲያገኙ በተለይም ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሥራ ያጡ ወጣቶች ቁጥር የትየለሌ ደርሶል ዶክተሮች፣ኢንጅነሮች፣ ወዘተ ሥራ ካጡ ሰነበቱ፡፡ ለሃገራችን የተማሩ ሰዎች ሥራ በአንደኛ ደረጃ ተጠያቂ  ከ1966 ዓ/ም ጀምሮ በሃገራችን የተተከለብን  የፖለቲካ ካድሬ ሥርዓት የተማረ ኃይል በእውቀትና በክህሎት  ሥራ የሚይዙበት ሥርዓት በመዘጋቱ ፖለቲከኞች ያለእውቀት ሥልጣን የጨበጡበት ዘመን በመሆኑ ነው፡፡ በደርግ  ዘመን ሰማንያ ሽህ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ካድሬዎች ነበሩ፡፡ በወያኔ ኢህአዴግ ሰባ ሽህ የህወሓት ካድሬዎች ነበሩ፡፡ በኢህአዴግና በኦህዴድ ብልፅግና ላለፉት ሠላሣ አመታት አስር ሚሊዮን ካድሬዎች የሥርዓቱ የደሞዝና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞች ከመደበኛው ባጀት  ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ካድሬዎች ሥርዓት አብቅቶ ከዩኒቨርሲቲ ምሩቆች በውድድር ሥራ የሚይዙበት ስርዓት እስካልመጣ ድረስ በምንም ዘዴ አዲሱ ትውልድ የሥራ ዕድል አያገኝም እንላለን፡፡ መንግሥዊ መዋቅር (State Machinery) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጣልቃ ገብነት እስካልተላቀቀ ድረስ የየክልሉ የፖለቲካ ካድሬዎች የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን በጀት ይዘው እንደማይደለድሉና እንደማይቀጥሮቸው የሠላሳ አመታት ታሪካዊ መረጃ ያሳያል፡፡ አስር ሚሊዮን የፖለቲካ ካድሬዎች በመንግስታዊ ቢሮክራሲ ውስጥ በመሰግሰግ መደበኛው በጀት በ2013/ ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት 476 (አራት መቶ ሰባ ስድስት) ቢሊዮን ብር ውስጥ 133 (መቶ ሠላሣ ሦስት) ቢሊዮን ብር  መደበኛ በጀት የተደለደለ ነበር፡፡ 2014/ ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት 561.67(አምስት መቶ ስልሣ አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ሚሊዮን) ብር ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች 162 ቢሊዮን ብር፣  መያዙ ተገልጿል። የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን በዚህ በጀት ውስጥ አለመካተታቸው ነው ሃገራችን ያሉ ወጣቶች ሥርዓቱን ለመቀየር ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ አመፅ የሚያቀጣጥሉት ………….(3)

 

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣውን በሃገራችን የሚገኙ የስራ አጥ ቁጥርን ልብ እንድትሉ ይረዳል፡፡ ከ18-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ወጣቶች ያሉበት የኢኮኖሚ ሁኔታ/ ከ18-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ወጣቶች ብዛት በክልሎችና በከተማ መስተዳደሮችችና የፈንድ ገንዘብ (ብር 10 ቢሊዩን) ድርሻ እናስተውላለን፡፡ …………(3)

 • በአፋር ክልላዊ መንግሥት 618,827 (ስድስት መቶ አስራ ስምንት ስምንት ሽህ፣ መቶሃያ ሰባት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 206 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በትግራይ ክልላዊ መንግሥት 1,578,463 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ስምንት ሽህ አራት መቶ ስልሳ ሦስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣527   ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በአማራ ክልላዊ መንግሥት 8,024,773 (ስምንት ሚሊዮን ሃያ አራት ሽህ ሰባት መቶ ሰባ ሦስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 2ቢሊዮን 679 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት 1,806,539 (አንድ ሚሊዮን ስምንት ሜ ስድስት ሽህ አምስት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣603 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 10,314,270 (አስር ሚሊዮን ሥስት መቶ አስራ አራት ሽህ ሁለት መቶ ሰባ ) የሥራ  አጥ  ይገኛሉ፣ 3ቢሊዮን 439 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት 338,433 (ሦስት መቶ ሰላሳ ስምንት ሽህ አራት መቶ ሠላሳ ሶስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 113 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በደቡብ ክልላዊ መንግሥት 5,643,731 (አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ሦስት ሰባት መቶ ሠላሳ አንድ) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 1ቢሊዮን 882 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት 150,414 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ አራት መቶ አስራ አራት) የሥራ  አጥ  ይገኛሉ፣ 50 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በሐረሪ ክልላዊ መንግሥት 80,259 (ሰማንያ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) የሥራ  አጥ  ይገኛሉ፣ 27 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በአዲስ አበባ ክልላዊ መንግሥት 1,255,486 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ሽህ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 419 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በድሬዳዋ ክልላዊ መንግሥት 164,762 (አንድ መቶ ስልሳ አራት ሽህ ሰባት መቶ ስልሳ ሁለት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 55 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • ጠቅላላ ድምር 29,975,958 (ሃያ ዘጠኝ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስምንት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 10 ቢሊዮን ብር ተመድቦ ነበር

ምንጭ፡- የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ (አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

ከኢትዮጵያ ህዝብ 70 በመቶ ወጣቶች ሲሆኑ፣ መጪውን ህይወታችሁን ለማስተካከል የሥራ እድል ይፈጠርላቸው እንላለን፡፡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመንደፍ ለብዙ ሚሊየን  ወጣቶች የሥራ ዕደል ይፈጥራል የምንለው ለዚህ ነው? የፕሮጀክቱ ጥናት ለሙያተኞች ቀርቦ ሃሳብ ሳይሰጥበት፣ ለህዝብ ቀርቦ ለሚሰራው ሥራ የህዝብ መሆኑን ሳይመክርበት ከላይ ወደ ታች መወርወር ሊታረም ይገባል እንላለን፡፡ ምሁራንም በዚህ ጉዳይ ሃሳባችሁን ለህዝብ እንድታካፍሉ፣ ከሆነ በኃላ እንዲህ ቢደረግ ኖሮ ከሚል ስለ ፕሮጀክቱ በጎና ጎጂ ሁኔታዎችን መግለፅ ሙያዊ ግዴታ አለባችሁ እንላለን፡፡አንድ ፕሮጀክት ስኬታማነት የሚገመገመው በከተማዋ ውስጥ ያሉትን ሥራ አጥ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል ያሰገኘላቸው እንደሆነ ነው፡፡  ለሠላሳ ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ እድል ከአሁኑ ጀምሮ ካልተጀመረ የሥራ አጡ ቁጥር ከአመት አመት እየጨመረ መሄዱ ወጣቶችን ለባህር ማዶ ስደት ይዳርጋቸዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ተቀማጭ ገንዘብ

#4-‹‹የፋይናንስ ተቋማት ገና ብዙ ሥራ ይጠብቃቸዋል የሚለውን ለማጉላት በአሁኑ ወቅት በአገር ደረጃ እየተሰጠ ያለውን ብድር ጠቅሰዋል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵ ንግድ ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ ወደ 668 ቢሊዮን ብር ተሰባስቧል፡፡ ከዚህ ተቀማጭ ገንዘብ ውስጥ ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ከአዲስ አበባ የተሰበሰበ ነው፡፡ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ተደምረው የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 35 በመቶ ብቻ ድርሻ ያለው ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው የፋይናንስ ተደራሽነት ሥራው ገና ብዙ የሚቀረው መሆኑን ነው፡፡›› የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ በአዲስ አበባ 434 ቢሊዮን ብር ሲሆን በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች 234 ቢሊዮን ብር ተሰባስቧል፡፡ በአዲስ አበባ ባለሃብቶች ሁለት ሦስተኛው የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን የባንኩ መረጃ ያሳያል፡፡ ህወሓት ኢህአዴግም ሆነ ኦህዴድ ብልፅግና  የኢትዮጵ ንግድ ባንክ በመቆጣጠር አዲስ አበባን ኃብትና ንብረት ቼዝ ኤንድ ቼክ የሚሎት፡፡

 

በአዲስ አበባ የተሰጠው ብድር

#5-‹‹ከብድር ጋር በተያያዘም አሁን ያለው አጠቃላይ ይዘት ምን እንደሚመስል ባመለከቱበት ገለጻቸው፣ የተሰጠው ብድር ትልቅ ዕድገት ማሳየቱን ነው፡፡ የብድር ምጣኔ ዕድገቱ በ13 በመቶ ጨምሮ 777 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ የፋይናንስ አገልግሎት አሁንም ከተማ አካባቢ በመሆኑ፣ ከተሰጠው ብድር ውስጥ ወደ 68 በመቶው ለአዲስ አበባ የተሰጠ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ማሰባጠር ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን እየተሰጠ ያለው የብድር መጠን እያደገ መጥቷል፡፡ እስከ በጀት ዓመቱ ዘጠነኛ ወር መጨረሻ ድረስ ለግል ዘርፉ የተሰጠው ብድር 273 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ይህ ከዛሬ ዓመት በፊት 81 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ የብድር አሰጣጡ ወደ ግል ዘርፉ ያደላ መሆኑን፣ ››……………..(4)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠው ብድር በአዲስ አበባ 528 ቢሊዮን ብር ሲሆን በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች 249 ቢሊዮን ብር ብድር ተሰጥቶል፡፡ በአዲስ አበባ ባለሃብቶች ሁለት ሦስተኛው የተሰጠው ብድር እንደሆነ የባንኩ መረጃ ያሳያል፡፡ ህወሓት ኢህአዴግም ሆነ ኦህዴድ ብልፅግና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቆጣጠር ለአዲስ አበባን ባለኃብቶች የሚሠጠውን ብድር  ቼዝ ኤንድ ቼክ የሚሎት፡፡ አዲስ አበባ ማለት የኢትዮጵያ ሃብትና ንብረት ሲሆን፣ አዲስ አበባ የአንድ ፓርቲ የኦህዴድ/የኦዴፓ ብልፅግና ኃብትና ንብረት ማድረግ ግን በፍፁም አይቻለም፡፡

 

ኦሮሙማ ማኒፌስቶ

‹‹ለምሳሌ 1: በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ተቋማት የፌደራሉም ሆነ የከተማ አስተዳደሩ ቋንቋቸው በህግ ሳይፀድቅ ኦሮምኛ እየሆነ ነው። “ህገመንግስቱ” ሳይሻሻል ለምን ይህ ሆነ ካልክ በድፍረት እኛ ተረኞች ነን ወይም ልዪ ጥቅም ይገባናል የሚልህ ገልቱ አታጣም።

ምሳሌ 2: አደስ አበባ የምትጠቀመውን ውሃ ከኦሮሚያ በሜትር ኩብ ህዝቡ እንዲከፍል የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ ይገኛል። ስለሆነም አዲስ አበቤው ለሚቀዳው ውሓ ለኦሮሚያ ለልዪ ጥቅም መብት ይከፍላል ማለት ነው።

ምሳሌ 3: የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮምኛ ቋንቋን እንዲያስተምሩ ገዳጅ ተጥሎባቸው ማስተማር ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል።

ምሳሌ 4: በአዲስ አበባ የሚገኙት የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የፌዴራል መንግስቱ አንዳንድ ተቋማትና የሰራተኛ ማህበራት የባንክ ቡካቸው በኦሮሞ ባንኮች ብቻ እንዲሆኑ ከተደረገ ቆይቷል።

ወዘተ …”ህገመንግስቱ”  አማራውን በይበልጥ እንደሚያጠቃ የተረዳው ኦሮሙማ ይሻሻል ሲባል እንደ ነብር ይሆንና በጎን ግን ሀይል ሁሉ የኛ ነው በሚመስል መልኩ ይከበር የማሉትን “ህገመንግስት” አሽቀንጥረው እየጣሉ የሚፈልጉትን እየሰሩ ቀጥለዋል። አሻሽለውታል ማለት አይደለም?››……………….(5)

 

ምንጭ፡-

 

Leave a Reply