“ኢንቨስት ኢን ፖቨርቲ ኢኒሼቲቭ” የተባለ የቢዝነስ ሞዴል ይፋ ተደረገ።ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በዛሬው እለት ኢንቨስት ኢን ፖቨርቲ ኢኒሼቲቭ የተባለውን ኘሮጀክት አስ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/tjxTL79EJXJjCBeHaywKGAWbuQiplYE6-CV_mmGfbfTNxU9eURnkyTFBppT6EJTOBNIXVbvEWMsSVi1LfZKiMDC7-yfREdvmpIp5qTRwGtncNSU-CcgOXk0TfjdFwYTqsw1jO1BbSi9-8U83RILooolwqBvWJmsBQQ3qJNMCatEtjfaT3Gb3dpL8qG9r_9lleZheuZStMK51L0IyTcuDVkYoyNV3xIL1dNvzW5eFJhadq0cAp1L45ywQ3loX8Xq_4rqRrNersnzUZTrgqTdwIJcuvb1ciHzk8aajeHCKVrLCqu8DHmvLwjFm2TrNvIczblo5dNyMzGTVlD7IEheO8g.jpg

“ኢንቨስት ኢን ፖቨርቲ ኢኒሼቲቭ” የተባለ የቢዝነስ ሞዴል ይፋ ተደረገ።

ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በዛሬው እለት ኢንቨስት ኢን ፖቨርቲ ኢኒሼቲቭ የተባለውን ኘሮጀክት አስተዋውቋል።

ይፋ የተደረገው ይህ አዲስ ሞዴል ለሀገራችን እንዲሁም ለአፍሪካ ትልቅ ትሩፋት መሆኑን የፐርዝ ብላክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ተናግረዋል።

የኘሮጀክቱ ዋና አላማም የብዙ ገበሬዎችን ህይወት መቀየር መሆኑን አንስተዋል።

የአካባቢውን አርሶ አደሮች ከገበያ ጋር በማስተሳሰር ኑሯቸውን ማሳደግ እና በመሃል ላይ ያለውን የተንዛዛ አሰራር በመቀየርና ደላሎችን በማስቀረት አምራቾች የሚያገኙትን ገቢ የሚያሳድግ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

አሁን ላይ አብዛኛው ገበሬ ከሚያመርተው ምርት ላይ ከ5-10 በመቶ የሚሆነውን ብቻ እየተጠቀመ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ “ከቢሊዮኖች ወደ ትሪሊየኖች” የሚል ሀሳብ መያዙንም በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ ተነስቷል።

ድህነትን በዘላቂነት እና ስልታዊ በሆነ መንገድ መቅረፍም ሌላኛው አላማው መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ያለንን ሀብት አብረን እናሰባስብ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በተሻለ አቅም እንዲያመርቱ የተለያዩ ድጋፎችን ከማድረግ ጀምሮ ጠንካራ የገበያ ትስስር ተፈጥሮላቸው በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍልም ምርቶችን በተመጣጠነ ዋጋ እንዲያገኝ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በሐመረ ፍሬዉ

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply