ኢን-ጆይ  በርገር ለአራት  የበጎ አድራጎት ድርጅቶች  የእርዳታ ድጋፍ አደረገ፡፡ላለለፉት 13 አመታት የፈጣን ምግቦችን(Fast food chain) በማቅረብ አገልግሎት  ላይ የተሰማራው ኢን-…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Hs6iHVPaqUvQKXrWneHXJqKY0-WmnQRaNi4Bl5UxQTBmMYYuTl8e3K8rQ595NrDlW0ogbUfWFE8tu3EE2YRlDzd6RNCNgkfh0qUQQmRr4Ok-3w8DfE3Sf_ylKBrynVcD313-olV3-70sR483m-4-FY4vTtARqMqwlle3tOAt509iJlyYl037Thm1G_8GUjylTnIgKpXXKFOmArBHhvji1FfFZWlxQv7Iq2qkT8Fc81VSLkIWusrArRvzpxM09DSeZfN6JHdaCmk1_sXjQ33Ig6216mNDKlJU8C40SiLheBZ-W2NKeY1ifGjN1a3Jdqhj-yNYeb_LlUgy_7eNSNfizQ.jpg

ኢን-ጆይ  በርገር ለአራት  የበጎ አድራጎት ድርጅቶች  የእርዳታ ድጋፍ አደረገ፡፡

ላለለፉት 13 አመታት የፈጣን ምግቦችን(Fast food chain) በማቅረብ አገልግሎት  ላይ የተሰማራው ኢን-ጆይ  በርገር ህፃናትን እና አረጋውያንን በማገዝ   ለተሰማሩ  ለ አራት  የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እርዳታ የሚውል የአንድ ሚሊየን ብር  የበጎ አድራጎት ድጋፍ በትናንትናው እለት አድርጓል፡፡

ሜሪጆይ ኢትዮጲያ   ፤ መሰረት ፋውንዴሽን  ፤  ሙዳይ በጎ አድራጎት እና ጎንደር ከተማ ለሚገኘው  ለቀድሞ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መርጃ ድርጅት ለእያንዳንዳቸው የሁለት መቶ ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ   ተበርክቶላቸዋል፡፡

ኢን-ጆይ በርገር    ላለፉት   ሁለት ወራት በሁሉም ቅርንጫፎቹ ህፃናት ልጆችን እና አዋቂዎችን  የሚያሳትፍ   የክረምት በርገር ፌስቲቫልን   አከናውኗል።

በዚህ የሁለት ወራት ፌስቲቫል ማጠናቀቂያ  ላይ ነው  ለአራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች  በድርጅቶቻቸው የሚያደርጉትን   በጎነት ለማበረታት እና ድርጅቱ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው ፡፡

በዚሁ የስጦታ ዝግጅት ላይ የተገኙት የበጎ አድርጎት  ተቋማቱ ተወካዮችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከተመሠረተ 13 አመታትን ያስቆጠረው ኢን-ጆይ በርገር  ስምንት ቅርንጫፎችን ከፍቶ  አገልግሎቱን  እየሠጠ ሲሆን  ከ350 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች ቋሚ የሥራ እድል ፈጥሯል።

በቅርብ ጊዜ ፍራንቻይዝ ለመጀመር ዝግጅት ላይ መሆኑን ያስታወቁት   የድርጅቱ ባለቤት እና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳለአምላክ አንዳርጌ  በቅርቡ ከኢትዮጵያ ውጪ አዲስ ቅርንጫፍ ለመክፈት ዝግጅት መጠናቀቁን ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

Source: Link to the Post

Leave a Reply