
በቅርቡ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ባንክ እንዲመሩ አቶ ማሞ ምሕረቱ መሾማቸው ይታወቃል። በአገሪቱ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት በናረበት እንዲሁም በአሜሪካ ዶላር እና በብር መካከል ያለው የምንዛሪ ዋጋ ልዩነት እየሰፋ ባለበት ጊዜ መሾማቸው ከባድ ጊዜ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ። በተጨማሪም በዚህ ፈታኝ ወቅት ለዚህ ወሳኝ ኃላፊነት በዘርፉ የካበተ ዕውቀት እና ልምድ ያለው ባለሙያ መመደብ ያስፈልጋል በሚል ሹመቱ በስፋት መነጋገሪያ ሆኗል።
Source: Link to the Post