ኢዜማ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ መግለጫ ሰጠ!! /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 17/2013 ዓ.ም ባህርዳር የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዜጎች በነፃነት ሀሳባ…

ኢዜማ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ መግለጫ ሰጠ!! /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 17/2013 ዓ.ም ባህርዳር የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዜጎች በነፃነት ሀሳባ…

ኢዜማ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ መግለጫ ሰጠ!! /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 17/2013 ዓ.ም ባህርዳር የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዜጎች በነፃነት ሀሳባቸውን የመግለፅ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል ብሎ ያምናል። እነዚህ መብቶች በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትም በግልፅ የተደነገጉ መብቶች ናቸው። የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 2 እንዲህ ይነበባል። «ማንኛውም ሰው ያለ ማንም ጣልቃገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው። ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በስነጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውም ዓይነት መረጃ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጫ ነፃነቶችን ያካትታል።» አንቀፅ 30 ንዑስ አንቀፅ 1 እንዲህ ይነበባል፦ «ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው» የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ከተማ ዜጎች ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል። መንግሥት ይህን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ እንደማይቻል አስታውቋል። በሕገ መንግሥቱ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው ይህ መብት ፈቃጅና ከልካይ የሌለው መብት ሆኖ ሳለ መንግሥት እራሱን ፈቃጅ እና ከልካይ አድርጎ ይህን በሕገ መንግሥቱ የተደነገገ መብት መጣሱ አግባብ አይደለም። ሰሞኑን ገዢው ፓርቲን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፎች በተከታታይ እየተደረጉ ባለበት ሁኔታ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለሚመለከተው የመንግሥት አካል በግልፅ በደብዳቤ ያሳወቀውን ሰላማዊ ሰልፍ መንግሥት በሚዲያ ወጥቶ መከልከሉን ማሳወቁን በጥብቅ እናወግዛለን ሲልም ገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply