ኢዜማ እና የምርጫ ቦርድ ዉሳኔየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ). ሰኔ 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ በቀረ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/JYKwmEKC23-A0hcWCB3Y1BT0zmGyXKCbMgHQCFmPKgVpDF1IugHUqjMZgdnaUPiZ14RvBc2YS8QTol3Trqpo0ORlP3rLPtC4sR75SxRKbx7XiiazLrbLHpfRwqo6P3MNPVEYnCO0LPVjiBXMxeEmE4o4fR1tRx7SL2p2K9Vrm7F2uMSlyVDbmG1jTbHehMt6y5pza48CUkeklub3Gl7yt33m1D_FVQ8L6MhS-9Nw35l4q-Py21Uyu2fK7EruWqOoNFF5VlMWHKdnT4Jr7iKK-vOvwBTQqZ-EwGLM3eACBrFDg1pRY-26tMBlrlLcqJGhNqndRyNMLXo993V5UWAaow.jpg

ኢዜማ እና የምርጫ ቦርድ ዉሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ). ሰኔ 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ በቀረቡለት አቤቱታዎች ላይ ውሣኔዎች አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ አባል የሆኑት እነአቶ ዘመኑ ሞላ (ስድስት ሰዎች) ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ ፓርቲው ሰኔ 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ባከናወነው 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የተለያዩ የደንብ ጥሠቶች ተፈጽመዋል በማለት ለቦርዱ ሰኔ 21 እና 29 እንዲሁም ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ያቀረቡትን አቤቱታ ለማጠናከር ይረዳል ያሉትን ተጨማሪ ማስረጃዎችን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል እነአቶ ደሳለኝ በዛብህ (ሁለት ሰዎች) እንዲሁ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ተመሳሳይ አየቱታ አቅርበዋል፡፡

ሆኖም ቦርዱ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ጠቅላላ ጉባዔው ሲደረግ ተፈፅመዋል ያሏቸውን ጥሠቶች በቅድሚያ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ተመልክቶ ውሣኔ ለመስጠት ስልጣን ላለው ሕግ ተርጓሚና አስፈጻሚ ኮሚቴ ጉዳዩን በማቅረብ እንዲፈታና ውሣኔ እንዲያገኝ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

በመሆኑም ለሕግ ተርጓሚና አስፈጻሚ ኮሚቴ አቤቱታቸውን እንዲያቀርቡ፤ አቤቱታው ለሕግ ተርጓሚና አስፈጻሚ ኮሚቴ ቀርቦ ውሣኔ ያገኘም ከሆነ ውሣኔውን ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ቦርዱ ነሀሴ ቀን 2014 ዓ.ም በአደረገው ስብሰባ ወስኖ ለአቤቱታ አቅራቢዎቹ አሳውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply