ኢዜማ የዴሞክራሲ የአደረ አፋሽ !!! የዴሞክራሲ ምሶሶዎች ተናዱ፣በንጉሥ አጫዎቾች!!! ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ

በአገራችን ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ምሶሶዎች የህግ አውጪ፣ የህግ ተርጎሚ፣ ህግ አስፈፃሚና ሚዲያ ሥር እየሰደዱ እንደ ቆጥኝ እየፀኑ ይሄዳሉ ሲባል በዘመናይ ልጆቾ እየዘመሙና እየተናዱ መሄዳቸው ምስጢር እንቆቅልሽ ሆኖል፡፡ የኢትዮጵያችን ማህፀን በሾተላይ ተጠቃና   ውርጃ እጣ ፈንታዋ ሆኖል!!!

‹‹በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመሥረት ወሳኝ ምዕራፍ በሆነው ቀጣዩ ምርጫ፣ የኢዜማ አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ ሕግን አክብራችሁ ፍፁም ሰላማዊነት እና ጨዋነት የተሞላበት የምርጫ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባችኃል፡፡›› ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣የዘመኑ የንጉሥ አጫዋች፡፡

በዓለም ዓቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቁ የስብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና የጦር ወንጀሎች፣ የዘር ማፅዳት ፍጅቶች በእውነትም ወይም በእውሽትም የሚሞግቱ የዓለም ዓቀፍ ሚዲያ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚዲያ ጦርነት ከፍተዋል፡፡ ዘ ጋርዲያን፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ቢቢሲ፣ ፎሬን ፖሊሲ፣ ሮይተርስ፣ አልጀዚራ ዜና ዘጋቢዎች (1) በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ትግራይ፣ ኦሮሚያ(ወለጋ)፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ) የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መቆረጥ (2) የስብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ወደ ትግራይ እንዳይገቡ መድረግ (3) የኤርትራ መንግስት መከላከያ ሠራዊት በኢትዮጵያ ትግራይ ጦርነት መሳተፍ (4) በትግራይ ክልል የሚገኝ የሽመልባ የኤርትራዊያን ስደተኞች መጠለያ ካንፕ በጦርነቱ መውደምና የኤርትራዊያን ስደተኞች ታፍኖ መወሰድ (5) የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ የርሃብ ፖለቲካ በመተግበር አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ለርሃብ አደጋ መጋለጥ ወዘተ በተለይ የጅምላ ግድያ፣ የማይካድራ የዘር ፍጅት፣ ፆታዊ ጥቃቶች፣ ስደተኞችን አግቶ መውስድ  የመሳሰሉት ዜናዎች በዓለም ዓቀፍ ሚዲያ እየተራገቡ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጰያ መንግሥት ስለ ሁኔታው ማስረዳት አልቻለም፡፡ ኢትዮጵያ በአልሰለጠኑ አንባሳደሮችና የዲፕሎማት ሹሞች ችሎታ ማነስ ለዓለም ማስተባበል ተስኖታል፡፡  የፖለቲካ ሣይንስና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ትምህርት ያልቀሰሙ ቅውቀት አልባ ጡረተኞችን አንባሳደር ማድረግ ያመጣው ጣጣ የትየለሌ ሆኖል፡፡

  • የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት የወጡ ህጎች ውስጥ ማንኛውም የፌዴራል መንግሥት ሹማምንት ከኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ እውቅና ውጪ በአገር ውስጥና ውጭ ሀገር የመንቀሳቀስ መብታቸው ታግዶል
  • በኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነትና የጋዜጠኞች መታሰርና መገደል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ሲፒጄ አስታውቆል፡፡ በትግራይ የጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አርአያና የጎደኛው በረከት በርሄ ግድያ በነፃና ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዲመረመር ጥያቄ ቀርቦል፡፡ Nairobi, January 28, 2021 — Ethiopian authorities must conduct a thorough and independent investigation into the killing of journalist Dawit Kebede Araya, determine if it was motivated by his work, and hold those responsible to account, the Committee to Protect Journalists said today. In the evening of January 19, unidentified attackers shot and killed Dawit, a reporter with the state-owned broadcaster Tigray TV, and his friend, Bereket Berhe, while they were driving near Dawit’s home in Mekelle, the capital of the northern state of Tigray, where conflict broke out in late 2020, according to news reports and four people familiar with the case who spoke to CPJ on the condition of anonymity, citing fear of retaliation. Dawit and Bereket were found in the car the next morning with gunshot wounds to their heads, and were buried later that day, according to Reuters. (Reporter Dawit Kebede Araya shot and killed in Ethiopia – Committee to Protect Journalists (cpj.org))
  • ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ስልጣን ከጨበጠ ሦስት አመት ሊሞላው ትንሽ ሲቀረው በሃገሪቱ የታሰሩ ጋዜጠኖች  ከስልሳ በላይ ሆኖል፡፡ ለናሙና ኤልያስ ገብሩ፣ተመሥገን ደሳለኝ፣ መድሃኔ እቁበሚካኤል፣ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማኝዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብር፣ ምስግናው ከፈለኝ፣ ኮሊንስ ጁማ ኦሴሞ (ኬንያዊ)፣ መለስ ድሪብሳ፣ ጉዬ ዋሪዬ፣ መሃመድ ሲራጅ፣ ቫብሳ አብዱል ከሪም፣ ደሱ ዱላ፣ ዋቆ ኖል፣ እስማኤል አብዱልራዛቅ፣ የአውራ አምባ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ፣ ወዘተ በ2020 እኤአ ብልጽግና ፓርቲ ጋዜጠኞችን በማሰር ከቻይና፣ ኢራን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ባይላሩስ፣ ኢትዮጵያ  ቀጥሎ ትገኛለች፡፡ በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመሥረት ወሳኝ ምዕራፍ በሆነው ቀጣዩ ምርጫ ይለናል ኢዜማ የንጉስ አጫዋች!!!   ምንጭ (http:// cpj.org/ Africa/Ethiopia/2020)
  • የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣  አስቴር ስዩም፣ ወዘተ   እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ምርጫ ላለመሳተፍ የምርጫ ካርድ እቀባ ለማድረግ እንገደዳለን በማለት ገለታው ዘለቀ  አሳስበዋል፡፡ የኦፌኮ አመራሮችም ጁሃር መሃመድና በቀለ ገርባ በእስር ቤት ይገኛሉ፣ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ቢሮዎቻቸው ተዘግተዋል ከአስር ሽህ አባላቶቻቸው መታሰራቸውን ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በመግለፅ በቀጣዩ ምርጫ በዚህ ሁኔታ ላለመሳተፍ እንገደዳለን ብለዋል፡፡  የኢዴፓ መሪ ልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት ለቆቸው ፖሊስ አለቅም በማለት ለስድስት ወራቶች ታስረው ተለቀዋል፡፡ ኢንጂነር ይልቃል ታስረው ተለቀዋል፡፡ በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመሥረት ወሳኝ ምዕራፍ በሆነው ቀጣዩ ምርጫ ይለናል ኢዜማ የንጉስ አጫዋች!!!
  • ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የመሰብስብና ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት ከ 2011 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ታግዶል፡፡ በቅርቡም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ታግዶል፡፡ በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመሥረት ወሳኝ ምዕራፍ በሆነው ቀጣዩ ምርጫ ይለናል ፕሮፌሰረር ብርሃኑ ነጋ!!! የዴሞክራሲ ያአደራ አፋሽ መሆኑን ዘንግቶት፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ
    ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ጋር ተዳብሎ፣ የደቡብ ምዕራብ ክልልን መመስረት ለመወሰን የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሚከናወን አስታውቆል፡፡ በደቡብ ክልል ህዝብ የደቡብ ምዕራብ ክልል ምስረታን ህዝብ ተወያይቶ አምኖበታል ወይ ወይስ ከላይ የተጫነበት ነገር ከሆነ ግጭት ይፈጥራል እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የክልልነትና የማንነት ጥያቄ በደቡብ ክልል የሲዳማ ክልላዊ መንግስትነት አስረኛ ክልላዊ መንግሥትነትን አፅድቆል፡፡ የወላይታ የማንነት ጥያቄ ህዝባዊ አመፅ ቀስቅሶል፣  የተሠው የሲዳማና ወላይታ ተወላጆች ፍጅት የትላንት ትውስታ ሲሆን ነገ ደግሞ በሌሎቹ አስራ ሁለት የሚደርሱ የክልል አስተዳደርና የማንነት ጠያቂዎች መቀጠላቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሃገሪቱ አጠቃላይ መፍትሄ መፈለግ አለባት ይህም ከዘር ፌዴላሊዝም የአደረጃጀት ሥርዓት ተላቀን፣ ከዘር ፖለቲካ ወጥተን የሚያባላንን የወያኔ ህገ-መንግሥት መከለስና መቀየር፣ የክልሎች ድንበርና ወሰንን በማጥፋት፣ ህዝቡ በፈለገበት ቦታ የመኖር ነፃነቱ፣ ተዘዋውሮ የመሥራት ነጻነቱ ሊረጋገጥለት ይገባል እንላለን፡፡
  • የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተደጋጋሚ በማይካድራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን የአማራን ዘር ማፅዳት ወንጀል፣ በወለጋ በኦነግ የዘር ፍጅት እንዲሁም በደቡብ ክልል ኦሞና በቤንች ማጂ ዞኖችና በጋምቤላ ክልል እየተፈፀሙ ያሉ የስብዓዊ መብት ጥሰቶች የብልፅግና መንግሥት ኃላፊነትና ተጠያቂነት መውስድ አልቻለም፡፡ በመላ ሃገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ጥስት አሳሳቢ ደረጃ ደርሶል፡፡ የብልፅግና ፓርቲ የሃገሪቱን ሰላምና ፀጥታ ማስጠበቅ ኃላፊነቱን መወጣት አልቻለም፡፡ የፀጥታ አካላት በህግ ተጠያቂነትም አልተረጋገጠም፡፡  በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ምርጫውን ለማድረግ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አለመረጋጋት እያለ በምርጫው ተጨማሪ ግጭቶች ተቀስቅሰው የሰዎችልቂትና የህዝብ መፈናቀል ይከሰታል የሚል ስጋት እንዳለን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እናሳስባለን፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክርቤቶች ምርጫዎች እንደሚፈፀሙ አስታወቆል፡፡ ግንቦት 28 ቀን የመረጡት ዳግም ሰኔ 5 ቀን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ምርጫ ላይ እንዲመርጡ የተቀናጀ ሴራ ነው ለሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቀናት ምርጫውን ለምን ማድረግ እንደፈለገ  የሚሠጠው ምላሽ ውኃ አያነሳም፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተቌማቱ ዝግጁነትና ገለልተኛነት፣ የታዛቢዎችና የምርጫው ሂደት ታዓማኒነት፣ የብሔረሰቦች የማንነት ጥያቄዎችና ከምርጫ ክልል ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎች፣እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችና የሚዲያ ሚዛናዊነትና ተዓማኒነት፣ ምርጫው ውጤት ጋር ተያይዘው ሊነሱ የሚችሉ ጉዳዩች አፈታት በዝርዝር አልቀረበም፡፡

 

ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቱ ይከበር!!!

ያለ ሕግ ልዕልና ዴሞክራሲ አይሰርፅም!!!

ያለ ሠላም፣ ፀጥታና  አስተማማኝ  የህዝብ ደህንነት ምርጫ ግጭት ያስከትላል!!!

Leave a Reply