
ከሳምንት በፊት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ፓርቲያቸው አስታወቀ። በአማራ ክልል ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት የፓርቲው ሊቀመንበር በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው መረጃዎች እንዳገኘ ፓርቲው ሰኞ መስከረም 21/ 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
Source: Link to the Post