ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን በድጋሚ የፓርቲው መሪ አድርጎ መረጠ

ሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ትናንት ሰኔ 26 ቀን 2014 ባካሄደው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ፕርፌሰር ብርሀኑ ነጋን የፓርቲው መሪ አድርጎ መርጧል።

ፓርቲው በየዘርፉ ተፎካካሪ እጩዎች ቀርበው የምረጡኝ ቅስቀሳ ካደረጉ በኋላ አሸናፊዎቹን እኩለ ሌሊት ገደማ ያሳወቀ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት (ፕ/ር) ብርሀኑ ነጋን መሪ እንዲሁም አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንን ምክትል መሪ አድርጎ መርጧል፡፡

እንዲሁም (ዶ/ር) ጫኔ ከበደ እና (ዶ/ር) አማኑኤል ኤርሞን ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

በተጨማሪም ኢዜማ አበበ አካሉን ዋና ፀሀፊ አድርጎ የመረጠ ሲሆን፤ በሚስጥር በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት በሌሎችም ዘርፎች ፓርቲውን የሚመሩ አባላትን ጭምር መርጦ መሰየሙን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply