ኢድ አልፈጥር እየተከበረ ይገኛል 1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ባህርዳር:- ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም……

ኢድ አልፈጥር እየተከበረ ይገኛል 1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ባህርዳር:- ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ታላቁን የረመዳን ወር ለ30 ቀናት ዱኣ በማድረግ፣ በሰላት እና ጾም በመጾም ያሳለፈው ህዝበ ሙስሊሙ የጾም መገባደጃ ምልክት የሆነችው ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ ዛሬ ኢድ አልፈጥርን በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ይገኛል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአደባባይ እና ከዚያም በኋላ ከቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጎረቤቶቻቸው ጋር በመሆን በዓሉን ያከብራሉ፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ስታድየም የዕምነቱ ተከታዮች በኢድ ሰላት ለማክበር እየተሰባሰቡ ይገኛሉ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply