ኢጋድ በአሁኑ ወቅት ቀጠናዊ ውህደት ላይ ትኩረት አድርጓል – ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ

ኢጋድ በአሁኑ ወቅት ቀጠናዊ ውህደት ላይ ትኩረት አድርጓል – ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ኢጋድ በአሁኑ ወቅት ቀጠናዊ ውህደት ላይ ትኩረት ማድረጉን አስታወቁ፡፡

ዋና ጸሐፊው ይህንን ያሉት ለኢጋድ የአምባሳደሮች ኮሚቴ ፣ ከመላው አካባቢ ለተውጣጡ የኢጋድ ሰራተኞች፣ ለአባል ሃገራቱ ዜጎች ፣ ለልማት አጋሮች ባደረጉት ዓመታዊ የቪዲዮ ኮንፍረንስ ላይ ነው፡፡

ዋና ጸሐፊው ንግግራቸውን የጀመሩት በቀድሞ የደበብ ደቡብ ሱዳን መስራች በሆኑት በጆን ጋራንግ “አፍሪካውያን እንደ አህጉር ሳይሆን እንደ ሀገር አንድ መሆን አለባቸው” በሚለው ነበር፡፡

ዋና ጸሐፊው በ2020 የኮቪድ ወረርሽኝ፣ የአንበጣ መንጋ እና ጎርፍ ለአባል ሃገራቱ ስጋት እንደነበሩ ጠቅሰዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ኮቪድን ሲከላከሉ ለነበሩ መስዋዕትነት ለከፈሉ የጤና ባለሙያዎች ታስበዋል፡፡

ኢጋድ ወረርሽኙ መከሰቱን ተከትሎ ለአባል ሃገራቱ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሰዋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የአባል ሃገራቱ መሪዎች እና ባለስልጣናት የተሳተፉበትን በኮቪድ ላይ ያተኮረ  ቪድዮ ኮንፍረንስ አስታውሰው ÷ ቀጠናዊ የኮቪድ ስትራቴጅ ከዚያ መመንጨቱንም ተናግረዋል፡፡

በወረርሽኙ እስካሁን ከ250 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ኮሮና ቫይረስ መያዛቸውንና እንዲሁም 5 ሺህ የሚሆኑት የአባል ሃገራቱ ዜጎች ህይወታቸውን እንዳጡ ነው የገለጹት፡፡

በቀጠናው የተከሰተው የአንበጣ መንጋም በ25 ዓመታት ውስጥ ያልታየ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚያም ባለፈ በቀጠናው 50 ሚሊየን ህዝብ የምግብ ዋስትና አደጋ ተደቅኖበት እንደነበር ጠቅሰው÷ ይህም በአባል ሃገራቱ ከሚገኙ ከአምስት ሰዎች ውስጥ አንደኛውን እንደሚያጠቃ  ነው ያታወሱት፡፡

ለአባል ሃገራቱ ፈተና ሆነው ከቆዩት መካከል ሦስተኛው ጎርፍ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ጸሐፊው 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡

በጎርፍ ጉዳት ከደረሰባቸው በሚሊየን ከሚቆጠሩት የአባል ሃገራቱ ዜጎች ውስጥ 700 ሺህ የሚሆኑት ከቀያቸው መፈናቀላቸውንም ነው  የገለጹት፡፡

ዶክተር ወርቅነህ አያይዘውም ይህ ሁኔታ የአየር ንብረት ለውጥ የደቀነው ትልቅ ፈተና ነው ሲሉ  አስረድተዋል፡፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ኢጋድ በአሁኑ ወቅት ቀጠናዊ ውህደት ላይ ትኩረት አድርጓል – ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply