ኤርትራውያን ስደተኞች ከህግ ውጪ እየታሰሩ ነው አለ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ፡፡ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያየ ግዜ ከህግ ውጪ በዘፈቀደ እየታሰርን ነው ሲሉ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶ…

ኤርትራውያን ስደተኞች ከህግ ውጪ እየታሰሩ ነው አለ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ፡፡

ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያየ ግዜ ከህግ ውጪ በዘፈቀደ እየታሰርን ነው ሲሉ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ቅሬታ ማቅረባቸውን ጣብያችን ሰምቷል፡፡

አቶ መብሪህ ብርሃነ የህግ ባለሙያ እና ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ሀገር በቀል የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ዳይሬክተር ናቸው፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በዘፈቀደ እየታሰርን ሲሉ አቤቱታ ይዘው ወደነሱ እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡

ለድርጅቱ ከህግውጪ በሆነ መንገድ እስሮች እየተፈፀመብን ነው የሚሉ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች እንደሚደርሱትም ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ተብሎ የሚጠራው ተቋም ከስደተኞች ጋር ተያይዞ አገልግሎት ማቆሙን ተከትሎ እንደዚህ ቀደሙ ስደተኞች ምዘገባ እና መንቀሳቃሻ ማገኝት ባለመቻላቸው ምክንያት እየታሰሩ ሊሆኑ እንሚችሉ ይታሰባል፡፡

ከዚህም ባለፈ በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ሳቢያ በክልሉ የነበሩ አራት ገደማ የስደተኛ መጠለያ ካምፖች በመውደማቸውና ስደተኞቹ ወደ ሀገር ሲገቡ የሚመዘገቡበት ሲስተም ባለመኖሩ ያለፍቃድ ለመንቀሳቀስ ተገደዋል የሚል ግምት እንዳላቸው ዳይሬክተሩ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የስደተኞች፣ የፍልሰተኞችና የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ክፍል ዳይሬክተር፤ እንጉዳይ መስቀሌነ ኢትዮ ኤፍ ኤም አናግሯል፡፡

ዳይሬክተሯም በተመሳሳይ ለነሱም ተደጋጋሚ አቤቱታዎች እየደረሳቸው እንደሚገኝና ምርመራ እየተካሄደ በመሆኑ ሙሉ መረጃ መስጠት እንደማይችሉ ለጣብያችን የተናገሩ ሲሆን አቤቱታውን መሠረት አደርገው የተደራጀ ቡድን ምርመራውን በቅርብ ይፋ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መብሪህ ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ስደተኛ ሆነው የመኖር መብታቸው ሊከበር ይገባል በቁጥጥር ስር ከዋሉም በህጉ መሠረት ለህግ ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ ለጣብችን ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ታህሳስ 30ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply