ኤርትራ ለጦሯ የክተት ጥሪ አደረገች

https://gdb.voanews.com/F353E78E-6371-4CD6-8395-AEE003C65AC1_w800_h450.jpg

ኤርትራ ለጦሯ የክተት ጥሪ ማድረጓንና የኢትዮጵያን መንግስት ከህወሃት ጋር እያደረገ ላለው ጦርነት ለመርዳት ልታንቀሳቅስ ይመስላል ሲሉ መንግስታት በመግለጽ ላይ መሆናቸውን  የኤ.ኤፍ.ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የክተት ጥሪውን ተከትሎ፣ ዜጎቻቸው በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የእንግሊዝና የካናዳ መንግስታት ባወጡት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አስታውቀዋል።

“የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት ተከትሎ በኤርትራ ያሉ የየአካባቢው ባለስልጣናት ለሃገሪቱ ጦር አባላት አጠቃላይ ጥሪ አድርገዋል” ሲል የካናዳ መንግስት አስታውቋል።

“በመላ ሃገሪቱ ተጨማሪ የህንነት እገዳዎች ካለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሊተገበሩ ይችላሉ” ሲል የካናዳ መንግስት ጨምሮ አስታውቋል።

የእንግሊዝ መንግስት የክተት ጥሪው ረቡዕ መደርጉን ገልጾ ዜጎች ተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል።

ህወሃት ባለፈው እሁድ በአፍሪካ ህብረት ለሚደረግ ድርድር ፈቃደኛ እንደሆነ ሲገልጽ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለህወሃት መግለጫ ቀጥተኛ መልስ ባይሰጥም፣ በሕብረቱ ለሚደረግ የሰላም ንግግር ዝግጁ እንደሆነ ቀደም ብሎ ሲገልጽ ቆይቷል።

ካለፈው መጋቢት ጀምሮ ለአምስት ወራት ጋብ ብሉ የነበረው ጦርነት ነሃሴ 17 2014 ሲያገረሽ፣ ገጭቱ በሰላማዊ መንገድ ይፈታል የሚለውን ተስፋ አደብዝዞታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply